ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Animals . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 09-08-18, 07:32 am


Karma: 90
Posts: 822/879
Since: 02-29-16

Last post: 66 days
Last view: 66 days
ከአጥቢዎች ውስጥ በዋነኛነት ግመሎች የበረሃ ነዋሪዎች ናቸው፡፡ ሁለት ዓይነት ግመሎች አሉ፡፡ አንዱ ባለአንድ ሻኛ ሌላው ባለሁለት ሻኛ፡፡ አብዛኞቹም በቀደመው የዱር ኑሮ ውስጥ አይደሉም፡፡ የሁለቱም ሻኛ ከውልደት በኋላ ቀስ በቀስ ከዕድሜያቸው መጨመር ጋር እያደገ የሚሄድ ነው፡፡ ግመሎች ሻኛ ከሌላቸው ላማ (Llama) ጋር በፊት ቅርፃቸውና እግራቸው ምክንያት መመሳሰላቸውን በማየት ዝምድናቸውን ማስተዋል እንችላለን፡፡

ውኃ ጥም?

ግመሎች በበረሃ ውስጥ ከ8 - 9 ቀናት ያለ ውኃ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ እስከ 34 ቀንም የቆዩ ግመሎች ተመዝግበዋል፡፡ ግመሎች ይህን ለማድረግ የመቻላቸው ምስጢርም ሻኛቸው ውኃን በስብ መልክ ለማከማቸት ስለሚያስችላቸው፣ የአካል ሙቀታቸው ከ34 ዲ.ሴ.ግ - 40 ዲ.ሴ.ግ. ምንም ሳይሆን መዋዠቅ ስለሚችል እና 40 ከመቶ ከሚሆነው የአካል ክብደታቸው ላይ የውኃ እጦት ቢፈጠርም መቋቋም በመቻላቸው ነው፡፡ በንፅፅር ስናይ ሰው ጤነኛ ሊሆን የሚችለው 37 ዲ.ሴ.ግ. ላይ የሙቀት መጠኑ ሲስተካከል ሲሆን 12 ከመቶ ከሚሆነው የአካሉ ክብደት በላይ የሚሆን ውኃ ካጣ ለመኖር ያዳግተዋል፡፡ በተጨማሪ ግመል ቶሎ ቶሎ የማያልበው መሆኑም አስተዋጽኦ ያደርግለታል፡፡ ላብ እንዲያመነጭ የአካሉ ሙቀት 40 ዲ.ሴ.ግ. መድረስ ይኖርበታል፡፡ ያም በላብ የሚያወጣውን የውኃ መጠን ይቀንስለታል፡፡

የተለያዩ የዱር አራዊት ለምሳሌ ቀጭኔ፣ የደጋ በግ፣ ፍየል፣ የዱር ከብት ብዙ ቀን ያለ ውኃ በመቆየት ይታወቃሉ፡፡ አንዳንድ የበረሃ ዝርያዎች ደግሞ ጭርሱኑ ውኃ እንደማይጠጡ ይታወቃል፡፡ እነኚህም፣ የሜዳ ፍየል፣ የምድር አደሴ ቁኒ (Ground squirell) እና ካንጋሮ አይጦች (Kangaroo rats) ናቸው፡፡

ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004 ዓ.ም.)

Pages: 1