ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Education - ትምህርት. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-06-18, 12:33 am (rev. 1 by Ye Arada Lij on 07-06-18, 12:33 am)


Karma: 90
Posts: 794/887
Since: 02-29-16

Last post: 183 days
Last view: 183 days
ለተመራቂ ተማሪዎች አምስት ጠቃሚ ነጥቦችተመራቂዎች እንኳን ደስ ያላችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ የሚለው ህብረ ዝማሬ ሲሰማ በትምህርት አለም ለቆየ የሚፈጥረው ስሜት አለ።
ለአንዳንዱ ስሜቱ ከእግር ጥፍር እስከ ራስ ፀጉር ድረስ የሚነዝር ነው። ለአንዳንዱ ወደ ኋላ የሚመልስ። ለበርካቶች ደግሞ የተማሪነት ህይወት የሚያበቃበት ደወል ነው።
እንዲህም ተባለ እንዲያ የምርቃት ቀን ልዩ ናት።
የበርካታ ዓመታት ጥረት ዕውቅና የሚሰጥበት ዕለት! ከዚህም በላይ ደግሞ ተመራቂ ተማሪዎች ወደሌላኛው የህይወት ምዕራፍ የሚሸጋገሩበት ቀን ነው።
ማንም የማይክደው ሀቅ ደግሞ ለስራ ዝግጁ የመሆን የመጀመሪያው ደወል ነው።
በያዝነው እና በቀጣዩ ወር በሺዎች የሚቆጠሩት ተማሪዎች ይመረቃሉ።በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በርካቶች ተመርቀው ስራ ማግኘት ቀላል አልሆነላቸውም።
ለሊሴ ብርሃኑ ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ትመረቃለች።
"ወደ ሥራው ዓለም ለመቀላቀል በዩኒቨርሲቲ ቆይታችን ወቅት ያስመዘገብነው ውጤት በሥራው ዓለም ስኬታም እንድንሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል''ትላለች።
በህንድ አገር የፑጃብ የኒቨርሲቲ የዶክትሬት ተማሪ እና በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የማሕበራዊ ስነ-አዕምሮ ተመራማሪ የሆኑት አቶ ዋቅቶላ ደምሰው አዲስ ተመራቂ ተማሪዎች የሚገጥማቸውን ፈተና እንዴት መወጣት እንዳለባቸው ያስረዳሉ።
አቶ ዋቅቶላ እንደሚሉት ከሆነ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች በሚኖሩባት አገር ለአዲስ ተመራቂዎች ስራ በቀላሉ ያገኛሉ ማለት ይከብዳል። ነገር ግን ቀጣዩቹ 5 ነጥቦች ወሳኝ ናቸው።


የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃ ማደራጀት


የአዲስ ተመራቂ ተማሪዎች የመጀመሪያው የቤት ሥራ የሚሆነው የትምህርት እና ክህሎት እንዲሁም የሥራ ልምድ ካላቸው በተሟላ መልኩ በሲቪያቸው ላይ መጥቀስ ነው።
ለሥራ ቅጥር ለጽሑፍም ይሁን ለቃለ መጠይቅ ፈተና ከመቅረባቸው በፊት የትምህርት እና የሥራ ማስረጃቸው አይቀሬ ነው።


ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት


መንግሥት ተመራቂዎችን በሙሉ ሊቀጥር የሚችል አቅም የለውም። ወይም የተመኘነውን የሥራ ዓይነት ማግኘት ቀላል አይሆንም። ስለዚህም ያለውን ውስን እድል ለመጠቀም ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል።
አቶ ዋቅቶላ ሲያስረዱ የቅጥር ማመልከቻ ከማቅረባችን በፊት ሥራው ምን አይነት ክህሎቶችን ይፈልጋል ብለን መጠየቅ አለብን።

መረጃ

የሥራ ቅጥር መረጃዎችን፣ ስለ ቀጣሪው ማንነት እና የምታመለክቱበት ስራው ስለሚፈልገው እውቀት እና ክህሎት በቂ መረጃ ይኑራችሁ።
ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ተለይቶ መገኘት
ከትምህርት ማስረጃችን በተጨማሪ ያመለከትንበት የሥራ ዘርፍ፣ ቀጣሪው ድርጅት የሚፈልገውን ክህሎት ማወቅ እና ይህንንም ለቀጣሪው ድርጅት በማሳየት የቅጥር እድላችንን ማስፋት እንችላለን።
የአዕምሮ ዝግጅት ማድረግ
በተማሪነት ዘመናችን ያሰብናቸውን እና ያለምነውን ማሳካት ላይሆንልን ይችላል። ለዚህም የአዕምሮ ዝግጅት ማድረግ ጠቃሚ ነው።
Pages: 1