ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Marriage & Divorce . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-05-18, 07:33 am


Karma: 90
Posts: 792/887
Since: 02-29-16

Last post: 206 days
Last view: 206 days
ባል እና ሚስቱ በመሀላቸው ግጭት ተፈጥሮ አይነጋገሩም፡፡ ሁለቱም በረጅም ትዝታ ተውጠዋል፡፡ መጀመሪያ ማውራት ሽንፈት መስሎ ስለታያቸው ሳይነጋገሩ መተኛ ሰዓታቸው ደረሰ፡፡
ድንገት ግን ባል የሆነ ነገር ትዝ አለው፡፡ ነገ በጠዋት የስራ ስብሰባ ለመታደም ወደዛ ለመሄድ በረራ አለው፡፡ ሁሌ ደሞ ወደ ስራ ሲሄድ እንቅልፋም በመሆኑ የምትቀሰቅሰው ሚስቱ ናት፡፡ እናም የነገው ስበሰባ እንዳያመልጠው ለሚስቱ "11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በአፉ መናገር ሞት መስሎ ታየው፡፡ እና ወረቀት ላይ "ነገ የስራ ስብሰባ ስላለበኝ ወደ ሌላ ሀገር እበራለው፡፡ አደራ 11 ሰዓት ቀስቅሽኝ" ብሎ በወረቀት ፅፎ እሷ የምታየው ቦታ አስቀምጦላት ምንም ቃል ሳይተነፍስ ተኛ፡፡
ጠዋት ሰውየው ከእንቅልፉ ሲነቃ ከጠዋቱ 3ሰዓት ሆኖ በረራውም ስብሰባውም አምልጦታል፡፡ "እንዴት እንደዛ አስጠንቅቄ ነግሪያት አትቀሰቅሰኝም?" ብሎ በጣም ተበሳጨ፡፡ ከአልጋው ለመነሳት ሲሞክር አንድ ወረቀት ኮመዲኖ ላይ ተቀምጦ አየ፡፡ "11 ሰዓት ሆኗል ተነስ ስብሰባ እንዳያመልጥህ" የሚል ፁፍ ተፅፎበታል፡፡
ማነው ስተት የሰራው? ማነው ልክ? ወዳጄ ሴትን ልጅ በተንኮልም ሆነ በፍቅር ልትበልጣት አትችልም፡፡ ዝምታ ደሞ መቼም መፍትሔ ሁኖ አያውቅም፡፡
♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦

Pages: 1