ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 1 guest | 4 bots
Pages: 1
Posted on 05-19-18, 06:35 am


Karma: 100
Posts: 666/751
Since: 03-20-17

Last post: 2 days
Last view: 2 days
በለጬዋ ሚስቴ ገለምሶ ሆነችብኝ
(ጫት ቅሜ ባላውቅም ሴት ልጅ ግን ሱስ ናት{ለማ መገርሳ ስታይል})
#ወንድማገኝ_ለማ
.
በቃ የሆነች ኮ ሰገጤ ነበረች። የዛሬን አያድርገውና እኔ ስጠብሳት ቀሚስ ባዲዳስ አድርጋ የቀጠርኳት ቦታ ስትመጣ ደሞዝ የተቀበለች አትሌት ነበር የምትመስለው! ዛሬ ግን የተገላቢጦሽ እኔ ፋሪቲ ሆኜላታለሁ። መቼለታ ቀጠሮ ስለነበረን ፂሜን በቀጭኑ ኦ(0) ተቆርጬ ወደሷ ጋ ስሄድ ጓደኞቿ ፊት...
"አፍህን ለምንድነው በክቡ የተኳልከው ?" አለችኝ
"ኧረ ኩል አይደለም ፂሜን በቀጭኑ ተቆርጬው ነው" ስላት
"እንዲህ አቅጥነኸው ታዲያ ለምን ተቆረጥክ?" አለችኝ
"ምነው ይደብራል እንዴ?"
"ኧረ አይደብርም ስታዛጋ እንዳይበጠስብህ ብዬ ነው "
አሁን እኔ ምን አፍ አለኝና ለሷ እመልሳለሁ? ዝም አልኳት። ያኔ ባናና ከመሆኗ በፊት ግን ሙድ መያዣዬ ነበረች። በታክሲ ስንሄድ
"ቶሎ እንድንደርስ ጋቢና ግቢ" ስላት አምናኝ ትገባ ነበር። ቁልምጫ እንኳን ስለማታውቅ "ወንድማገኝ ለማዬ" እያለች ነበረ በፍቅር የምትጠራኝ።
"ወይዬ" እላታለሁ
"እስቲ ቆንጆ በርገር ጋብዘኝ እኔ ቲፑን እዘጋለሁ " ትለኝ ነበር። የዋህነቷን ስለማፈቅረው እንደቃልሽ ይሁን እላት ነበር። ሺ ጊዜ ደጋግሜ የሰማሁት ቀልድ እንኳን ቢሆን እሷ አፍ ላይ ስሰማው ይጥመኛል። አንዴ እንዲህ አለችኝ....
"ብታይ ማታ ከደወልክልኝ በኋላ መኝታ ክፍሌ ውስጥ ቢንቢዎቹ ጥዝዝዝዝ እያሉ አላስቸገሩኝ መሰለህ?"
"....እ....ሺ...."
"እሺ ሳይሆን ምን አደረግሽ? ነው የሚባለው"
"እሺ ምን አደረግሽ"
"ቀስ ብዬ ካልጋ ላይ ተነሳሁኝና በሩን ከፍቼ በሃይል ዘጋሁት....ከዛ ቢምቢዎቹ ዝም አላሉ መሰለህ?"
"እንዴት?!"
"በሩን በሃይል ስዘጋው የወጣሁ መስሏቸው ኮ ነው " ለመቶ ምናምነኛ ጊዜ ብትነግረኝም ያወራችው እሷ ናትና እንከተከትላታለሁ
.
ከሆነ ጊዜ በኋላ ታዲያ
"የኔ ባቅላባ እውቀትሽን ለማስፋት መፅሐፍቶችን ማንበብ አለብሽ" እያልኩ ይሄንን ፍልስፍናና ሳይኮሎጂ መፅሐፍቶች ስግታት ተለዋወጠችብኝ አይገልፀውም። በቃ መግባባት ወፍ የለም! ውዝግብግብ አደረገችኝ። አልጋ ላይ ጋደም ብለን እኔ ጃክ እሷ ሮዝን ሆና ቁልት አድርጎኝ። ሁለነገሬ ከቆመብኝ በኋላ እንድትግልልኝ ብዬ በሹክሹክታ የፍቅርና የቅንዝር ቃላትን ሳዘንብላት....
"ለምንድነው ግን የምታንሾካሹከው?" ትለኛለች
"ጮክ ካልኩኝማ ስሜት አይሰጠንም ከሙድ እንወጣለን!" ስላት
"መጀመሪያ ነገር ግን ስሜት ምንድነው?" ትለኛለች
በደንፉ "ምን ዓይነት ጥያቄ ነው?!" እላታለሁ
"ምን አይነት ጥያቄ ነው ስትል ምን ማለትህ ነው?! ብዙ አይነት ጥያቄ አውቃለሁ ለማለት ነው? ወይንስ ጥያቄን
በጥያቄ በመመለስ ሀሳቡ ላይ እንድንመሰጥበት ፈልገህ ነው?" አስባችሁታል አልጋ ላይ ተጥደን እሷ ሴቷ ሶቅራጥስን ስትሆንብኝ ሁለመናዬ እንዴት እንደሚኮላሽ? ደግሞ መቼለት እንዲህ አለችኝ
"ሩካቤ ስጋ ከፈፀምን ግን ቆየን አይደል?" አለችኝ (ቃላቶቿ ራሱ ተቀይረዋል። ልጅቷ ከሚስትነት ወደ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ ዲክሽነሪነት ተቀይራለች። አጠገቤ ስትጋደም ራሱ ትልቅ መፅሐፍ አቅፌ የምተኛ ነው የሚመስለኝ)
"አዎ" አልኩ ሰፍ ብዬ
"አየህ ሩካቤ ስጋ መፈፀም ሰነፍ ያደርጋል። ስለዚህ ካሁን በኋላ እኔና አንተ ምንም አናደርግም!" ሰትለኝ አሲድ ደፍቼባት መፅሔት ላይ ዜና መሆን ራሱ አምሮኝ ነበረ።
"እኔ ና አንቺ ሴክስ ካላደረግን ባልና ሚስት መሆናችን ምኑ ላይ ነው?" ተንጨረጨርኩኝ አይገልፀውም
"ባልና ሚስት የግዴታ ሩካቤ መፈፀም አለበት እንዴ?"
"እና ታዲያ ሰው ለምንድነው የሚጋባው? ያምሻል እንዴ? ኧረ በፈጠረሽ መፈላሰፉን ተይና አርፈሽ ሚስት ሁኚ!" ብዬ ብመክር ባስመክር ወይ ፍንክች አለች።
" እስከመቼ ነው ግን ሴክስ የማናደርገው?" አልኳት
"ቢያንስ ለ5 ዓመታት"
"ከዛስ¿¿¿¿¿" ስላት
"ከዛማ ትለምደዋለህ" አላለችኝም።
ትለምደዋለህ ስትለኝ ትዝ ያለኝ ነገር ቢኖር ይቺ የሙጋቤ ጭዌ ናት "አፍሪካዊያን ወንዶች ወሲብ ላይ በአማካይ ለ30 ደቂቃዎች ያክል የሚቆዩ ሲሆን ነገር ግን 28ቱን ደቂቃዎች የሚያሳልፉት ሴቷን በመለመን ነው "
Pages: 1