ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Family. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 05-15-18, 07:39 am


Karma: 90
Posts: 782/848
Since: 02-29-16

Last post: 9 days
Last view: 8 days
#ባቡሬ_ቀርታብኝ

እንደየ ሁልጊዜው ማለዳ ነቅቼ ባቡሬን እየጠበኩ ነው። ዛሬ ለየት ያለብኝ የባቡሯ ሰአት መዘግየት ገርሞኛል። ሰከንድ ዘግይቶ የማያውቅ ነገር 7ደቂቃ ሲዘገይ እጅግ ያበሽቃል። እንዲያውም መሃል መሃል ላይ 'ብሽቅ!..' እያልኩ ሳላውቀው በሚኮሳተረው ፊቴና በንዴት ግራ እና ቀኝ ከሚላወሰው በድን አካሌ ጋር ላየኝ ፀብ ያማረኝ እመስላለሁ... ትንሽ ሳስበው 'የሽሮ ድንፋታ እስኪገነፍል' ነውና ዋ'ጥ አድርጌ ተረጋጋሁ። በ'ስተግራ በኩሌ እምታምር የነጣች ቆጆ ሴት እግሯን እጥፍ አድርጋ ስልክ እየጎረጎረች በግራ እጇ ጣቶች ያገተችውን ሲጋራ ትም..ገ..ዋ..ለች። ግን ቆንጆ ነች።
ትንሽ ከፍ ብሎ ትልቅ የጆሮ ማዳመጫ ጆሮው ላይ የደነቀረ አንድ የሚቅለሰለስ ወጣት አየሁ።Gey ነው መሰለኝ። ተመስጦ ስልኩን ይጎረጉራል። አብዛኛውን ስመለከተው ስልኩን ይጎረጉራል። እዚህ ሃገር ህዝቡ ኢንተርኔት የሚጠቀመው እንደሃበሻ አልጋላይ ተኝቶ አይደለም። ጊዜ የለውማ። እጁ ላይ ስልክ ሳይጨብጥ የሚሄድ ሰው ማግኘት ይከብዳል ። እኔም እየለመዳብኝ ነው ትላንት ወድያ አቀርቅሬ እየጻፍኩ ስሄድ ከአንድ አሮጊት ጋር ሳንተያይ አጠገብ ተደራርሰን ስለነበር ቀና ስንል ከንፈር ልንሳሳም ትንሽ ነበር የቀረኝ....አጋጣሚ ቀና ብዬ ስጠጋ አሮጊት ሆነች እንጂ... አሁን እዚህ አጠገቤ ላይ ያለችውን ልጅ ብትመስል ግጭታችን በከንፈር ቀይሬ ቀኔን በፍቅር ነበር ምጨርሰው... ብስማት ያለመተያየታችን ስለሚጎላ የሚከፋት አይመስለኝም። እና ምን ልል ነው ...ህዝቡ ግዜ ስለሌለው ስልክ ላይ ተኝቶ ነው የሚሄደው.. 'ፎቶሽን ላኪልኝ' ብትል እዛው ምንገድ ላይ ሰልፊ ተነስታ ትልክልሃለች። ወይ ደግሞ ቅዳሜ ማታ ካስጨፈራት ወንድ ጋራ የተነሳችውን ፎቶ ትልክልህ ይሆናል። ሃበሻ ተኝተን እንጠይቃለን እድሜ ይስጠን ብቻ።
ዙሪያዬን አጥርቼ ካየሁ ቡሃላ ነበር ስልኬን አውጥቼ ፌስቡክ በተባለ ጫጫታ መንደር ውስጥ የገባሁት። ከወትሮው ለየት ይላል እናት ያለውም የሌለውም ስለ እናቱ ይጽፋል ቀኑ "የ እናቶች ቀን" መሆኑ ነዋ። ሁሉም ለእናቱ ብዙ ይመኛል ብዙ ይኮመታል ብዙ like ይሰጠዋል። እኔም like ገጭቻለሁ። ለኔ ለእናት ስለተፖሰተ ነገር ከኮመንት ይልቅ ላይክ መስጠት በጥቂቱም ይሻለኛል። ምክንያቱም አይደለም ስለ እናቴ...... አለም ላይ ስላሉ ባ'እድ እናቶች እንኳ ፍቅሬን የምገልጽበት በቂ ቃላት የለኝምና ነው!።
ቆይ አንዴ ባቡሯ መጣች...
.
.
.
.
.
ብትዘገይም መጥታለች ባቡሬ 'ህውሃት አይደለች ቆማ የምትቀር መቼስ'
እናም እኔም ለምን ስለ እናቴ አልጽፍም አልኩ። በአለም ላይ በዚህ ጊዜ የምሳሳላት እናቴ ብቻ ናት! የኔ ችግር 'እማ እወድሻለሁ' ብዬ ሀሳቤን እንዴት ልጀምር እንደምችል ነው። የቱስ ቋንቋ ይሆን እናቴን የሚገልጽልኝ?? አናቴ ላይ ሲወርድ የነበረ ሃሩር ጸሃይና ከድንጋይ የከበደ በረዶ አናቴ ላይ ሲወድቅ በመቀነቷ ከልላኝ ያሳደገችኝን.... አይደለም ታምሜ ተደናቅፌ ወድቄ የምትራራ የምታለቅስ እናቴን በየትኛው ብዕር ለከትባት እችላለሁ? ከውቅያኖስ በላይ የገዘፈ ታሪኳንስ እጨልፈው ዘንድ እንዴት ይቻለኛል??? አንድ ቀን ውጭ ወጥቼ ማደሬ እሷን እንቅልፍ አሳጥቶ ሲያቃዣት ያደረውን ያንን እረጅም ለሊት እንዴት ልገልጸው እችላለሁ? ??
#እኔ_አይደለም_ስለ_እናቴ #ስለ_እናቶች_ የምገልጽበት ቋንቋ የለኝም።
ተጀምሮ የማያልቅ ነገር ለመጻፍ አስቤ ሳይሆን ሰዎች ጀምረው የማይጨርሱትን ነገር በመጻፋቸው ይህንን ጻፍኩት።
የወለዳችሁ ለመውለድ፣ በእርግዝና ላላችሁ ፣ በአምላክ ፍቃድ መውለድ ለተሳናችሁ፣ ወደፊት የምትወልዱ እናን'ተ ውብ ቆነጃጅቶች በሙሉ... የእናትነት ወጉ አላ'ችሁና እንኳን አደረሳችሁ መልካም የእናቶች ቀን ይሁንላችሁ ብያለሁ።
.
.
አይደለም እናንተን ቅድም ስታጨስ የነበረቿን ቆንጆ እንኳን ምርቃቴን ባደርሳት ደስ ብላኝ!። ደግሞ ሳልወዳት አይቀርም እስኪ ነገ ላግኛት
ሳገኛት ምን እንደማረግ ታውቃላችሁ....
.
.
.
በሉ መውረጃዬ ደርሻለሁ ማልጨርሰውን ጀምሬ 'መልካም የእናቶች ቀን!'
Pages: 1