ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Family. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 05-15-18, 07:39 am


Karma: 90
Posts: 781/848
Since: 02-29-16

Last post: 9 days
Last view: 8 days
#ባቡሬ_ቀርታብኝ

እንደየ ሁልጊዜው ማለዳ ነቅቼ ባቡሬን እየጠበኩ ነው። ዛሬ ለየት ያለብኝ የባቡሯ ሰአት መዘግየት ገርሞኛል። ሰከንድ ዘግይቶ የማያውቅ ነገር 7ደቂቃ ሲዘገይ እጅግ ያበሽቃል። እንዲያውም መሃል መሃል ላይ 'ብሽቅ!..' እያልኩ ሳላውቀው በሚኮሳተረው ፊቴና በንዴት ግራ እና ቀኝ ከሚላወሰው በድን አካሌ ጋር ላየኝ ፀብ ያማረኝ እመስላለሁ... ትንሽ ሳስበው 'የሽሮ ድንፋታ እስኪገነፍል' ነውና ዋ'ጥ አድርጌ ተረጋጋሁ። በ'ስተግራ በኩሌ እምታምር የነጣች ቆጆ ሴት እግሯን እጥፍ አድርጋ ስልክ እየጎረጎረች በግራ እጇ ጣቶች ያገተችውን ሲጋራ ትም..ገ..ዋ..ለች። ግን ቆንጆ ነች።
ትንሽ ከፍ ብሎ ትልቅ የጆሮ ማዳመጫ ጆሮው ላይ የደነቀረ አንድ የሚቅለሰለስ ወጣት አየሁ።Gey ነው መሰለኝ። ተመስጦ ስልኩን ይጎረጉራል። አብዛኛውን ስመለከተው ስልኩን ይጎረጉራል። እዚህ ሃገር ህዝቡ ኢንተርኔት የሚጠቀመው እንደሃበሻ አልጋላይ ተኝቶ አይደለም። ጊዜ የለውማ። እጁ ላይ ስልክ ሳይጨብጥ የሚሄድ ሰው ማግኘት ይከብዳል ። እኔም እየለመዳብኝ ነው ትላንት ወድያ አቀርቅሬ እየጻፍኩ ስሄድ ከአንድ አሮጊት ጋር ሳንተያይ አጠገብ ተደራርሰን ስለነበር ቀና ስንል ከንፈር ልንሳሳም ትንሽ ነበር የቀረኝ....አጋጣሚ ቀና ብዬ ስጠጋ አሮጊት ሆነች እንጂ... አሁን እዚህ አጠገቤ ላይ ያለችውን ልጅ ብትመስል ግጭታችን በከንፈር ቀይሬ ቀኔን በፍቅር ነበር ምጨርሰው... ብስማት ያለመተያየታችን ስለሚጎላ የሚከፋት አይመስለኝም። እና ምን ልል ነው ...ህዝቡ ግዜ ስለሌለው ስልክ ላይ ተኝቶ ነው የሚሄደው.. 'ፎቶሽን ላኪልኝ' ብትል እዛው ምንገድ ላይ ሰልፊ ተነስታ ትልክልሃለች። ወይ ደግሞ ቅዳሜ ማታ ካስጨፈራት ወንድ ጋራ የተነሳችውን ፎቶ ትልክልህ ይሆናል። ሃበሻ ተኝተን እንጠይቃለን እድሜ ይስጠን ብቻ
Pages: 1