ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Education - ትምህርት. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 05-08-18, 07:04 pm


Karma: 90
Posts: 775/848
Since: 02-29-16

Last post: 9 days
Last view: 8 days
የጨረራ ስነህይወታዊ ጠንቆች
/Biological Effects of Radiation/
• የጨረራ ስነህይወታዊ ጠንቆችን በዝርዝር ከመግለፃችን በፊት ስለጨረራ ምንነትና አይነቶች በጥቂቱ እናስቃኛችሁ፡፡ ጨረራ ምንድን ነው? ብለን ስንጠይቅ በኤሌትሮኒክ ማግኔቶች ሞገዶች ወይም በቅንጣጢቶች መልክ የሚፈጠር ጉልበት ወይም ሀይል ነው፡፡
• ጨረራን ለተለያዩ ለልማት ተግባራት ስንገለገል ከሚሠጣቸው ጠቀሜታዎች ባሻገር በሰው ልጅ በአካባቢ በአሁኑ እና በመጪው ትውልድ ላይ የሚያስከትለው ስነህይወታዊ ጠንቅ ቀላል አይደለም፡፡ አዎን ፈጣሪ የጨረራ ቁሶች የሰውን ልጅ ለጉዳት በማጋለጥ የሚስተካከላቸው የለም፡፡ጋማ፣አልፋ፣ፕሩቶን፣ኒውትሮን የመሣሠሉት በራዲዮ አክቲቪቲ አማካኝነት ሲፈበረኩ ከመጠን ካለፉ ወይንም ከለላ ካልተጠቀምን ከፍተኛ ጉዳቶችን ያስከትላሉ፡፡
ጨረራ በአጭርና በረጅም ጊዜ የሚያደርሣቸውን ስነህይወታዊ ጠንቆች በሁለት ምድብ ከፍሎ ማየት ይቻላል
• ጨረራ በአጭር ጊዜ የሚፈጥረው ጠንቅ ዲተርሚኒስቲክ ኢፌክት ሲባል ዋንኛ ምልክቶቹ ጊዜያዊ መሀንነት ፣የፀጉር መገሽለጥ፣ የቆዳ መላላጥ የአይን ግርዶሽ የሠውነት ማቃጠልና፣ከፍተኛ ማቅለሽለሽ ሲሆኑ የአጭር ጊዜ የጨረራ ስነህይወታዊ ጠንቆች ለትውልድ የመሸጋገር አቅም የላቸውም፡፡ይህ የሚከሠተው አንድ ሰው በከፍተኛ ሁኔታ ለጨረራ ሲጋለጥ ነው፡፡
• ሌላው የጨረራ ስነህይወታዊ ጠንቅ በረጅም ጊዜ የሚፈጠር ሲሆን እስቶካአስቲክ ተብሎ ይጠራል፡፡ የሚታዩ ዋና ዋና ምልክቶች ቋሚ መሀንነት የዲ ኤን ኤ /DNA/ እና አር ኤን ኤ/RNA/ መዛባት ካንሠር ከወሊድ በፊት የውርጃ ችግር የሚወለዱ ልጆች ተጣብቀው መወለድ እነዚህና ሌሎችም ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የእስቶክአስቲክ ኤፌክት ከትውልድ ትውልድ የሚሻገር በመሆኑ አደጋው እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡
Pages: 1