ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Food & Drink - ምግብ እና መጠጥ. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 03-03-18, 09:26 pm


Karma: 90
Posts: 751/887
Since: 02-29-16

Last post: 314 days
Last view: 314 days
1- ካሮት

ከ ካሮት ጥቅሞች መካከል የኮሌስትሮል መጠንን መቀነስ፣ የልብ ድካም አደጋን መቆጣጠር የተወሰኑ የ ካንሰር ዓይነቶችን መከላከል፣ የዓንን የእይታ መጠን ማጎልበት፣ እንዲሁም ያለ ዕድሜ የሚከሰቱ የእርጅና ምልክቶች እንዳይኖሩ ማድረግ የሚሉት ይካተቱበታል፡፡ ካሮት በውስጡ ጠቃሚ ቫታሚኖችን እና ፖታሺየም የተሰኘ የደም ግፊትን መቆጣጠር የሚችል ማዕድንን ይዟል፡፡ በተጨማሪም የ ካሮት ሰማንያ ስምንት በመቶ የሚሆነው ክፍል ውሃ በመሆኑ ለጤናማ ሰውነት ዓይነተኛ አማራጭ ነው፡፡

የካሮት የውበት ጥቅሞች

በካሮት ውስጥ የሚገኙት ቫይታሚኖች ለቆዳ ውበት እና ጤንነት በርካታ ጥቅሞችን ይሰጣሉ፡፡ ከዛም ውስጥ ጥቂቱን፡-

1- ብሩህ ቆዳ ይሰጣል
ካሮት በውስጡ ቫይታሚን ሲ ያለ በመሆኑ መርዛማ የሆኑ ውህዶችን ከሰውነታችን የማስወገድ ኃይል አለው፡፡ ስለዚህ ካሮት አብዝተን በምንመገብ ወቅት የሞቱ እንዲሁም ጤናማ ያልሆኑ ቆዳዎች ከላይችን ላይ እየተወገዱ እንዲመጡ እና ብሩህ እና አንፀባራቂ የሆነ ቆዳ እንዲኖረን ያስችላል፡፡
ካሮትን በመፍጨት እና ከማር ጋር በመለወስ በቤት ውስጥ ለፊት እንደማስክ መጠቀም የሚቻል ሲሆን ለቆዳ ብሩህነት ወደር የሌለው አማራጭ ነው ሲሉ የስነ ውበት ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

2- የእርጅና ምልክቶችን ያጠፋል
የቆዳ መሸብሸብ፣ ዓይን እና ከንፈር አካባቢ መኮማተር እና የመሳሰሉት የእርጅና ምልክቶች በዕድሜ የሚመጡ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ግን ፍሪ ራዲካል የተሰኙ ጎጂ ውህዶች በሰውነታችን ውስጥ በመበራከታቸው ምክኒያት ያለ እድሜም ይታያሉ፡፡ ካሮት በውስጡ እንደ ቫይታሚን ኤ እና ሲ ያሉ ፀረ መርዛማ ውህዶች ያሉት በመሆኑ የቆዳ መሸብሸብን እና መጨማደንን በመከላከል ውጥር ያለ እና አዲስ የሆነ ቆዳ እንዲኖር ያስችላል፡፡

3- እንደ ዣንጥላ ያገለግላል
ካሮት በውስጡ ቤታ ካሮቲን የተሰኘ ንጥረ ነገር ያለ በመሆኑ ህብረህዋስን በአዲስ በመተካት አላስፈላጊ በሆኑ የፀሀይ ጨረሮች የተጎዳውን ቆዳ የመተካት በሀሪ አለው፡፡ ከዛም በተጨማሪ የቆዳን እራሱን የመከላከል አቅም( immunity) በማሳደግ በፀሀይ ጨረር የተጎዳ እና የተጠበሰ ቆዳን ያክማል፡፡ በቋሚነት የካሮት ጁስን በቤት ውስጥ እያዘጋጁ መጠቀም የሚመከር ነው፡፡


2- ኪያር

በተለምዶ አትክልት እየተባለ የሚጠራው ይህ ኪያር የተሰኘ ተክል ፍራፍሬ እንደሆነ ሰምተው ያውቃሉ? ኪያር በውስጡ ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡ በተጨማሪም በውስጡ ከፍተኛ የሆነ የውሃ መጠን እና ዝቅተኛ የሆነ የካሎሪ መጠን ስላለው ሰውነትን ረስራሳ (hydrated) እንዲሁም ሸንቃጣ እንሚያደርግ ይታመናል፡፡
የኪያር የውበት ጥቅሞች ውስጥ ጥቂቱን፡-

1- ለሰውነት ርስራሴ(hydration)
ኪያር 95 በመቶ የሚሆነው ክፍሉ ውሀ ነው፡፡ ስለሆነም ሰውነታችን ውስት ሉ መርዛማ ውህዶች በመጠራረግ እና የደም ዝውውርን ጤናማ በማደረግ ለሰውነታችን በቀ የሆነን ፈሳሽ ይሰጣል፡፡ ይህ ደግሞ ጤናማ ለሆነ ውብ የሆነ ቆዳን ይሰጣል፡፡

2- ለ ፈካ ቆዳ
አሁን አሁን ቆዳን ለማፍካት የተለያዩ የኬሚካል ይዘታቸው ከፍ ያሉ ሜካፖችን መጠቀም የተለመደ ሆኗል፡፡ ይሁንና እነዚህ ኬሚካሎች ከጊዜ በኋላ የሚፈጠጠሩት የቆዳ ችግር በቀላሉ የሚታከም አይሆንም፡፡ ኪያር ውስጡ ያለው ንጥረ ነገር ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ ቆዳን ማፍካት የሚስችለው በመሆኑ በቤት ውስጥ በቀላሉ በማዘጋጀት መጠቀም ይቻላል፡፡

3- ለፀጉር እድገት እና ጤና
ኪያር በውስጡ በቂ የሆነ የ ሲልከን እና የ ሰልፈር መጠን ስላለ ጤናማ የሆነ የፀጉር እድገት እንዲኖር ይረዳል፡፡ ኪያርን በመፍጨት እና ውሃውን የራስ ቅል ውስጥ በመቀባት ከ 15-20 ደቂቃ ድረሰ አቆቶ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ ይመከራል፡፡


ለቀን ተቀን ህይወታችን እንት እንዴት እንጠቀማቸው?

2 የተፈቀፈቀ ካሮት፣ 1 ተለቅ ያለ ኪያር (ኪያሩን ሳንልጥ ቢሆን ይመከራል)፣ ቆራርጦ ጁስ መፍጫ ውስጥ ማድረግ ከዛ 1 ወይም 2 ብርቱካን ውስጡ መጭመቅ እስከ 4 ማንኪያ ድረስ እርጎ (እንዳስፈላጊነቱ ማካተት ካልሆነም መተው ይቻላል)ውስጡ መክተት፣ በስተመጨረሻም ሩብ ብርጭቆ ውሃ በማድርግ በደንብ መፍጨት እና መጠጣት፡፡

ማታ ሊተኙ ሲሉ አሊያም ጠዋት ከእንቅልፍ ሲነሱ ይህንን ጭማቂ ሁሌም በመጠጣት የውበትም የጤናም ተጠቃሚ ይሆናሉ ያለችን editorialnatualbeauty ናት፡፡


ያወቅነውን ማሳወቅ ቅንነት ነው፡፡

Pages: 1