ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Animals . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 02-14-18, 07:14 am


Karma: 90
Posts: 737/879
Since: 02-29-16

Last post: 93 days
Last view: 93 days
ኦፖሶም (Opposum)፣ ካንጋሮ (Kangaroo)፣ ካኦላስ (Kaolas)፣ የታዝማኒ ወልፍ (Tasmanian Wolf)፣ ውምባት (Wombat) እና ባንዲኮት (Bandicoot) ኪሴ አጥቢዎች ናቸው፡፡

እነዚህ አጥቢዎች አርጋዥ ባለ ኪስ (ከረጢት) ናቸው፡፡ ይህም ማለት እንስሳቱ አርግዘው የሚወልዱ ቢሆንም፤ የተወለዱት ልጆች በቂ ጥንካሬ ስለማይኖራቸው ከተወለዱ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ እናታቸው ሆድ ስር ያሉ ኪስ (ከረጢት) ውስጥ ይቆያሉ፡፡ በዚህም ምክንያት የርግዝና ወቅታቸው አጭር ነው፡፡ ተፈጥሮ ባለ ከረጢቶቹን አጥቢዎች በጣም አነስተኛ የሆኑ ያለጊዜው የሚወለዱ ልጆች እንዲኖራቸው ሲያደርግ፤ ልጆቻቸውን ረዘም ያለ የማጥባትና የወላጅ እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው ያደርጋቸዋል፡፡ ይህንንም እንክብካቤ ለማድረግ ከሆዳቸው ስር ያለው ከረጢት (ኪስ) ያገለግላቸዋል፡፡ ስለዚህ በቂ ምግብ አያገኝ የነበረው ሽል ከተወለደ በኋላ ከረጢቱ ውስጥ እንዳለ የተሻለ ዕድገት እስኪያሳይ ይመገባል ማለት ነው፡፡

ባለከረጢት አጥቢዎች ከካንጋሮና ኦፖሶምስ ቤተሰቦች በተጨማሪ የታዝማኒያ ዴቭል (Tasmanian Devil)፣ ባንዲኩት (Bandicoot)፣ የማርሱፒያል ወልፍ (Marsupial Wolf) እና ፈላንጀሮችን (Phalangers) ይይዛል፡፡ የእኒህ ቤተሰብ ሴቶች ከታችኛው የአካላቸው ክፍል ሥር ማርሱፒየም የሚባል ከረጢት መሳይ አካል አላቸው፡፡ ስማቸውም ‹‹ማርሱፒያል›› የተባለው በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ማርሱፒያሎች አውስትራሊያ ውስጥ የዚያ ብቻ ሆነው የሚገኙት፣ አህጉሪቷ እነሱን ከተቀበለች በኋላ በውኃ በተፈጠረው የምድር ክፍል ምክንያት ለሌሎች አጥቢዎች ዝግ በመሆኗ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ዓይነቱ የመልክ-ምድር አቀማመጥ (ውኃ፣ ተራራ፣ የመሳሰሉት) እንስሳቱን ከአሉበት አካባቢ ወደሌላ አልፈው እንዳይሄዱና በአሉበት ተወስነው እንዲቆዩ፣ ርባታቸውም እርስ በርስ ብቻ ሆኖ በጊዜ ሂደት ከሌሎች ጋር የተለዩ በመሆን ላሉበት አካባቢ የዚያ ብቻ እንዲሆኑ ምክንያት ይሆናል፡፡

ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004 ዓ.ም.)

Pages: 1