ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Animals . | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 02-14-18, 06:16 am


Karma: 90
Posts: 736/879
Since: 02-29-16

Last post: 93 days
Last view: 93 days
የኤሊ ዝርያዎች በየብስም በውኃም ውስጥ ይኖራሉ፡፡ በሴል የተሸፈኑ መሆናቸው ከሌሎች ገበሎ አስተኔዎች ይለያቸዋል፡፡ በዓለም ላይም 300 ያህል ዝርያዎች እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ ኤሊዎች ጥርስ አልባ ናቸው፡፡ ይህ ግን ከምንም ነገር አያግዳቸውም፡፡ ይልቅስ በሚገባ የሚጠቀሙበት በጣም ስል የሆነ አጥንታም ግንጭል አላቸው፡፡ ይህም ከአመጋገብ ልምዳቸው ጋር የተጣጣመ ሥራ አለው፡፡ ባያኝኩም ምግቡን ይዞ ለመቦጨቅ ያገለግላቸዋል፡፡ ምግቡ ስለማይታኘክም እንዳለ ይዋጣል፡፡

ብዙ ኤሊዎች የእንስሳትም ሆነ የዕፅዋት ተዋጽኦ ይመገባሉ፡፡ አንዳንዶቹ የወፍ ዝርያዎች ይመገባሉ፡፡ ዋነኛ ምግባቸው ግን ቅጠል፣ አበባ፣ ቀንድ አውጣ፣ ዓሳና አፅቄ ናቸው፡፡ ትልልቆቹ ኤሊዎች ደግሞ የትኛውንም ዓይነት ሊይዙት የቻሉትንና ያሸነፉትን ይመገባሉ፡፡

ብዙዎቹ ኤሊዎች በከፊል ውኃ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ግን ለምሳሌ ትልልቆቹ የባሕር ዝርያዎች የብስን የሚያዩት ለጥቂት ጊዜ ለዚያውም በድርያ ወቅት ብቻ ነው፡፡ በአንፃሩ የብስ ላይ ብቻ የተወሰነው የሚኖሩትም ዝርያዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ በየአካባቢያችን የምናያቸው ኤሊዎች ጥቂቶቹ ውኃ ውስጥ ካልተገደዱ በቀር አይገቡም እንዲያም ሆኖ ባገኙት አጋጣሚ ወደ የብስ ይመለሳሉ፡፡

ሀ) አተነፋፈስ

በሳምባቸው የሚተነፍሱ ቢሆንም የጫናቸው ከባድ ሼል አተነፋፈሳቸውን ከባድ ያደርግባቸዋል፡፡ ለዚህም የእግርና ትከሻ ጡንቻቸውን መጠቀም አየር የማስወጣትና የማስገባት ተግባር ያከናውናሉ፡፡

ለ) አንጎል

እንደ ሌሎቹ ገበሎ አስተኔዎች ሁሉ የኤሊዎችም አንጎል በመጠን አነስተኛ ነው፡፡ የአካላቸውን ክብደት አንድ ፐርሰንት ያህል ቢሆን ነው፡፡ ሆኖም የመማር ክህሎታቸው እንደ አይጥ ከፍተኛ ነው፡፡ የማስማት ችሎታቸው አነስተኛ ነው፡፡ እሱን ግን በጥሩ የማሽተትና የማየት ክህሎት ያካክሱታል፡፡ የማየት ክህሎታቸው ቀለምን እስከመለየት ያደርሳቸዋል፡፡ በዚህም ከሰው ጋር ይመሳሰላሉ፡፡

ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004 ዓ.ም.)


Pages: 1