ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Animals . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 02-14-18, 06:09 am


Karma: 90
Posts: 733/879
Since: 02-29-16

Last post: 93 days
Last view: 93 days
ጃርቶች (Porcupines) ከሌሎቹ የአይጥ ዝርያዎች የሚለዩት እንደመርፌ በሾሉ ወስፌዎቻቸው ነው፡፡ እሱንም በመወርወር ከነሱ የተወሰነ እርቀት በመሄድ ወደነሱ እየተጠጋ ያለውን አጥቂ እንስሳ ቆዳ በመጉዳት እራሳቸውን ይከላከላሉ፡፡ እንደ መርፌ የሾሉ ወስፌዎቻቸውን ሲወረውሩ ግን ሆን ብለውና አውቀው ላይሆን ይችላል፡፡ ሆነም ቀረ ግን እነዚያ የሾሉ ወስፌዎች የመከላከያ ጥሩር ሆነው ከተለያዩ አዳኞቻው ይታደጓቸዋል፤ ለምሳሌ ከተራራ አንበሶች (Mountain Lions)፣ (Lynkes)፣ ኮዮቴ (Coyote) እና ሌሎችም አዳኞቻው፡፡

አንዳንዶቹ አዳኝ እንስሳዎች አፋቸውና ጉሮሯቸው ውስጥ የሾሉ ወስፌዎች ተገኝቶባቸዋል፡፡ እርግጥ ነው ፊሸር (Fisher) የተባለው የድመት ቤተሰብ ውስጥ የሚገኘው እንስሳ በጥንቃቄ እነዚህ ወስፌዎች የሌሉበትን የውስጠኛውን የሆድ ክፍል በማጥቃት ሊገለው ይችላል፡፡

ጃርቶች የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚያደርጉበት ጊዜ ሴቶቹ እኚህን የሾሉ ወስፌዎች ለወንዱ ጉዳት እንዳያደርስ አድርገው ራሳቸውን ለግንኙነት ያዘጋጃሉ፡፡ ስለዚህም ወንዱ በተፈጥሮው ሴቷ የግንኙነት ፍላጎት አሳይታ እስክትመጣ ድረስ ተረጋግቶ መጠበቅ ግድ ይሆንበታል፤ ከጉዳት ለመታደግ እንድትረዳው፡፡ ለሴቷ ጃርት ደግሞ ካልፈለገችው ግንኙነት ወስፌዋ ይታደጋታል ማለት ነው፡፡

ልጆቻው ሲወለዱም እኒዚህን የሾሉ ወስፌዎች ይዘው ቢሆንም አናታቸው ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ሲወለዱ ጠንከር ባለ መሸፈኛ የተሸፈነ ነው፡፡ ከዚያ ባለፈ ግን አወላለዳቸው እንደማንኛውም አጥቢ እንስሳ ነው፡፡

ማንይንገረው ሸንቁጥ፣ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004 ዓ.ም.)

Pages: 1