ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Animals . | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 02-14-18, 06:08 am


Karma: 90
Posts: 732/879
Since: 02-29-16

Last post: 93 days
Last view: 93 days
መርዛም እባቦች ይናደፋሉም፤ ያጠቃሉም፡፡ የንድፊያው ልክ የሚለያየው በእባቡ ዓይነት ነው፡፡ ረጅም ጥርስ ያላቸው እንደ ራትል እባብ (Rattle Snake) ዓይነት ዝርያዎች ብዙም አያኝኩም፡፡ አፋቸው በሚዘጋ ጊዜ ረጅሙ ቱቦ መሳይ ተንቀሳቃሽ ጥርሳቸው ታጥፎ ወደ ውስጥ ይገባል፡፡ አንድ እባብ በሚያጠቃበት ጊዜ አፉን ይከፍትና የታጠፈው የመርዝ መጨመሪያ ጥርስ (Fang) ለንድፊያ ይንቀሳቀሳል፡፡ ከዚያም ወደፊት በመወንጨፍ ጥርሱ የተጠቂውን ቆዳ አልፎ ሲገባ እባቡ ይናደፋል፡፡ በዚህ ንድፊያ ወቅት የሚያገለግለው ጡንቻ የመርዝ ከረጢቱ መርዙን እንዲያፈስ ያደርግና በቱቦ አማካይነት ክፍት ወደሆነው ጥርስ መጥቶ የተነከሰው ቁስል ላይ ይፈሳል፡፡ ጥቃቱ፣ ንድፊያውና ወደ ጥቅልል ሁኔታ አመላለሱ በጣም ፈጣን በመሆኑ እነዚህን እንቅስቃሴዎች በዓይን ለመከታተል ያስቸግራል፡፡ ሆኖም የአብዛኞቹ እባቦች የማጥቂያ ርቀት ብዙ ሰዎች ከሚያስቡት የራቀ ነው፡፡ እንደውም ሁለት ሦስተኛ የሚሆነው የአካላቸው ክፍል መሬት እንደያዘ ነው የተቀረው ክፍል ለጥቃት የሚወነጨፈው፡፡ እንደ ኮብራ ያሉት በጣም አጭር ጥርስ ያላቸው ደግሞ በሚነድፉበት ወቅት ለጥቂት ጊዜ ያዝ አድርገው ያኝካሉ፡፡ ይህ የእኘካ እንቅስቃሴ መርዙን ወደ ቁስል እንዲገባ ያደርገዋል፡፡ እንዲህ ዓይነቶቹ እባቦች ብዙም ጥቃት አያደርሱም፡፡ ልብስና የሸራ ጫማዎችን በማድረግ ብቻ ከጥቃታቸው መዳን ይቻላል፡፡ - ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004)

Pages: 1