ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 4 guests | 1 bot
Pages: 1
Posted on 02-02-18, 06:45 am


Karma: 100
Posts: 580/741
Since: 03-20-17

Last post: 26 days
Last view: 19 days
ሞዴል አርብቶአደሩን የ EBC ጋዜጠኛ ቤቱ ሄዶ ኢንተርቪ እያደረገው ነው ...
ጋዜጠኛ ፦ ፍየልህን ምንድነው የምትመግባት?
ገበሬው ፦ ጥቁሯን ነው ወይስ ነጯን?
ጋዜጠኛ፦ ነጯን
ገበሬው፦ ሳር ነው።
ጋዜጠኛ፦ ጥቁሯንስ?
ገበሬው፦ ያው ሳር ነዋ።
ጋዜጠኛ፦ እሺ ማደሪያዋስ የት ነው?
ገበሬው፦ ጥቁሯን ነው ወይስ ነጯን?
ጋዜጠኛ፦ ጥቁሯን።
ገበሬው፦ ከእርሻው ማዶ ባለው ክፍል።
ጋዜጠኛ፦ ነጯንስ?
ገበሬው፦ ያው አንድ ላይ ነው ማሳድራቸው።
ጋዜጠኛ፦ እሺ ለማጠብስ ምን ምን ትጠቀማለህ?
ገበሬው፦ ጥቁሯን ነው ነጯን?
ጋዜጠኛ፦ ነጯን።
ገበሬው፦ ውሃ ነዋ።
ጋዜጠኛ፦ ጥቁሯንስ?
ገበሬው፦ እሷንም ውሃ ነው።
ጋዜጠኛው፦ (በጣም ተበሳጭቶ)
ያምሀል እንዴ? ለሁለቱም ተመሳሳይ ነገር ከሆነ
ምትጠቀመው ለምን አስር ግዜ ጥቁሯ ነጯ እያልክ
ታደክመኛለህ?
ገበሬው፦ ምክኒያቱም ነጯ የኔ ናታ።
ጋዜጠኛው፦ ጥቁሯስ የማን ናት?
.
.
.
.
.
ገበሬው፦ በርግጥ ጥቁሯም የኔ ናት!
Pages: 1