ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 4 guests | 2 bots
Pages: 1
Posted on 02-02-18, 06:40 am


Karma: 100
Posts: 579/741
Since: 03-20-17

Last post: 26 days
Last view: 19 days
ድንዝዙ ሰው
...
የድንዝዙ ግራ እጅ ማሽን ወድቆበት
ተሰበረ ጓደኛዉ ሊጠይቀዉ ቤቱ ሄደ
"እግዜር ነዉ ያተረፈህ ቀኝ እጅህን
ቢሰብረዉ ኖሮ ስራ መስራት ያስቸግርህ ነበር" ቢለው
.
ድንዝዙ "እኔስ እሱን አዉቄ አይደል እንዴ ልክ ማሽኑ ሊወድቅ ሲል በፍጥነት
ቀኝ እጄን አንስቼ ግራ እጄን ያስቀመጥኩት"ብሎት እርፍ
...
ከብዙ አመታት በፊት ነዉ ድንዝዙ
ቺኩን "እንድንጋባ እፈልጋለሁ" አላት
"እርግጠኛ ነህ?"
"አዎ እርግጠኛ ነኝ"
"ግን እኮ አንድ አመት እበልጥሀለሁ"
"ኦዉዉ ልክ ነሽ በቃ የሚቀጥለዉ አመት እንጋባለን"ብሏት እርፍ
....
ድንዝዙ ለሚስቱ ይደዉልና
"ጉድ ሆኘልሻለሁ መኪናየን መሪዋን
ነዳጅ መስጫዋን ዳሽ ቦርዷን ማርሿን
በሙሉ ነቃቅለዉ ሰርቀዉኛል.."
ከዛ ጥቂት ቆይቶ መልሶ ደወለላት...
"...ይቅርታ የኔ ቆንጆ እየመጣሁ ነዉ ቅድም ለካ በሁዋላ በር ገብቼ ነዉ"
....
"ዶክተሩ ያዘዘልህን የአይን መድሃኒት
መጠቀም ጀመርክ" አለችዉ ባለቤቱ
"አልጀመርኩትም እባክሽ" አላት
ድንዝዙ
"እንዴ ለምን?"አለችሁ
"ዶክተሩን አላመንኩትም ምን ነካሽ በጠራራ ፀሀይ አይደል እንዴ ባትሪ
አብርቶ የመረመረኝ"
...
"Passwordህን አወቅኩት" አለዉ
ድንዝዙ Facebookሲከፍት ለነበረዉ
ጓደኛዉ
"እሽ Passworedu ምንድን ነዉ?"
ጠየቀዉ
ድንዙዝም መለሰ "በተከታታይ ስድስት ኮከቦች"
Pages: 1