ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Diet & Fitness . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 01-31-18, 06:26 am


Karma: 100
Posts: 402/426
Since: 07-12-15

Last post: 447 days
Last view: 447 days
የሞሪንጋ (ሽፈራው) ቅጠልና የሚሰጣቸው ጥቅሞች

በእኛ ሃገር `ሺፈራው` እየተባለ የሚጠራው ይህ ተክል የሆድ ህመምን ጨምሮ ለአለርጂ፣ ለልብ እና ተያያዥ ችግሮች፣ ለስኳር ህመም፣ ለቆዳ፣ ለፀጉር፣ መመርቀዝ (ኢንፌክሽንን) እና እብጠቶችን ለመከላከል እንደሚረዳ ይነገራል። የህክምና ባለሙያዎችም ከዚህ ያለፈ ጠቀሜታውን እንደሚከተለው ይዘረዝራሉ፤

1. አስምን ለማከም፦ ሞሪንጋ በአስም ምክንያት የሚከሰቱ አደገኛ አጋጣሚዎችን መቀነስና የጉሮሮ አካባቢን መጥበብ ችግር መቅረፍ ያስችላል። ከዚህ ጋር ተያይዞም የተስተካከለና ጤናማ የአተነፋፈስ ስርዓት እንዲኖር በማድረግ ጤንነትን ለመጠበቅ ይረዳል።

2. የሰውነት ላይ እብጠትና የፈሳሽ ክምችትን ያስወግዳል፦ ህመም የሚያስከትለውንና በሰውነት አካል የሚከሰት እብጠትን መከላከልም የዚህ ተክል ጠቀሜታ ነው። ፈሳሽ በአንድ የሰውነት አካል ላይ መጠራቀሙን ተከትሎ የሚከሰተውን ይህን እብጠት ለማከምም ይህን ተክል ከምግብ ጋር መጠቀም ይቻላል።

3. ለቆዳና ፀጉር ደህንነት፦ በውስጡ ከያዛቸው ፕሮቲኖችና ሌሎች ንጥረ ነገሮች አንጻር ሞሪንጋ የፀጉርና ቆዳ ጤንነትን ለመጠበቅ እጅጉን ይረዳል። ከዚህ ባለፈም የፀጉርን መነቀልና የቆዳ መድረቅን የሚከላከሉና የተፈጥሮ ወዝን የሚጠብቁ ንጥረ ነገሮችን በመያዙ እንደ ፀጸጉር መነቃቀልና የቆዳ መሰንጠቅና መድረቅ ያሉ ችግሮችን የመከላከል አቅም እንዳለው ባለሙያዎች ይናገራሉ። ቆዳ ላይ የሚከሰቱ ችግሮችንም ሆነ የፀጉር ደህንነትን ለመጠበቅ ይህን ተክል መጠቀም ይችላሉ።

4. ጉበትን ለማከም፦ በመጠጥም ይሁን በሌሎች አጋጣሚዎች ጉበት ላይ የሚከሰትን የጤና እክል ማከምም ከዚህ ተክል የሚገኝ ጠቀሜታ ነው። በመሰል አጋጣሚዎች ጉበት ከፍተኛ ጉዳት እንዳይደርስበት በማድረግ በቶሎ እንዲያገግምም ይረዳዋል።

5. ካንሰርን ለመከላከል፦ ይህ ተክል በውስጡ ካንሰርን ለመከላከልም ሆነ ካንሰርን ከመስፋፋት መታደግ የሚያስችሉ ንጥረ ነገሮችን የያዘ መሆኑ ይነገራል። ኒያዚሚሲን የተባለው ንጥረ ነገርም የካንሰርን እድገት መግታትና ካንሰርን መዋጋት የሚችል ሲሆን በሞሪንጋ ወይም ሺፈራው ተክል ውስጥ ይገኛል።

6. የሆድ ህመምን ለማከም፦ የሆድ መነፋትን ጨምሮ ምቾት ማጣትና የጨጓራ ህመም ስሜቶችን ማከም እንዲሁም የምግብ አለመፈጨትን ማስተካከልም ሌላው ጠቀሜታው ነው። በውስጡ የያዛቸው ፀረ ባክቴሪያና ፀረ ተዋህስያን ንጥረ ነገሮች የሆድ ውስጥ ህመምን ሲከላከሉ ቫይታሚን ቢ ደግሞ የስርዓተ ምግብ መፈጨትን ያስተካክላል።

7. ባክቴሪያ ወለድ በሽታዎችን ይከላከላል፦ ይህን ተክል ከሻይ ጋርም ሆነ ከሌሎች ምግቦች ጋር መጠቀምዎ ባክቴሪያ ወለድ በሽታዎችን ለማከምና ለመከላከል ይረዳዎታል።
8. ለአጥንት ጥንካሬ፦ ሞሪንጋ በውስጡ ካልሺየምና ፎስፎረስ እንደመያዙ መጠን ለአጥንት ደህንነትና ጥንካሬ እጅጉን ይረዳል። የመገጣጠሚያም ሆነ የእግርና የእጅ ላይ እብጠቶችንና መሰል ህመሞችን መከላከልም ያስችላል።

9. የስሜት መዘበራረቅን ለማስተካከል፦ ተክሉ በውስጡ ለሰው ልጆች አስፈላጊ የሆኑ በርካታ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ነው። በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚከሰቱና ለስሜት መዘበራረቅ መንስኤ የሚሆኑ፥ እንደ ድብርት፣ ጭንቀት፣ መረበሽና ከፍ ያለ ድካምን ለማከምና ለማስወገድ ይረዳል።

10. የልብ ጤንነትን ለመጠበቅ፦ የህክምና ባለሙያዎች የልብና ተያያዥ የጤና እክሎችን ማከምና ተጋላጭነትን መቀነስ የዚህ ተክል ጠቀሜታ መሆኑን ይገልጻሉ። ከዚህ አንጻርም የልብን ጤንነት ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ነው የሚገልጹት።

11. ቁስልን ለማከም፦ ሰውነት ላይ በተለያየ አጋጣሚ የሚከሰቱ ቁስሎችን ማከምና ጠባሳ እንዳይከሰት ማድረግም የዚህ ተክል ትሩፋት ነው። በደም ውስጥ የሚገኝ የግሉኮስ መጠንን መቀነስ ይችላሉ፤ በሽንት ውስጥ የሚገኝ የስኳር እና ፕሮቲን መጠን መቀነስም ያስችልዎታል። ይህ የተስተካከለ የኦክስጅን ዝውውር እንዲኖር በማድረግ የስኳር ህመም ተጋላጭነትን ያስወግዳል።

12. የደም ግፊትን ለመቀነስ፦ ሞሪንጋ አይዞቲዮሲያኔት እና ኒያዚሚኒን የተባሉ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ በብዛት ይዟል። እነዚህ ንጥረ ነገሮች ደግሞ በድንገት የሚከሰትን የደም ግፊት መጨመርን ለማስቆምና ለመከላከል የሚያግዙ ናቸው።

13. ምንጊዜም ቢሆን በተባለው ልክና መጠን መጠቀምንም አይዘንጉ። አሁኑኑ ሼር ያድርጉት

Posted on 11-02-18, 05:18 pm


Karma: 100
Posts: 2/3
Since: 11-02-18

Last post: 582 days
Last view: 577 days
tnx
Pages: 1