ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Diet & Fitness . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 01-31-18, 06:22 am


Karma: 100
Posts: 401/426
Since: 07-12-15

Last post: 339 days
Last view: 339 days
ውሃን ብቻ ብንጠጣ ምን ሊፈጠር ይችላል?

በየቀኑ የተለያዩ ፈሳሾችን ለመጠጥነት እንጠቀማለን፡፡ ጠዋት ከእንቅልፋችን ተነስተን ሻይ ምሳ ላይ ደግሞ ቡና እንጠጣለን፤ ብርጭቆአችንን በጭማቂ፣ በአነቃቂ ወይም በሀይል ሰጪ መጠጦች የምንሞላበት ቀንም ብዙ ነዉ፡፡ ነገር ግን እንደ እዉነቱ ከሆነ ለሰዉ ልጅ የሚሆነዉ ጤናማ መጠጥ ንፁህ ዉሀ እንደሆነ እናዉቃለን፡፡ ስለዚህ የሰዉ ልጅ ለመጠጥነት ከሌሎች ፈሳሾች ይልቅ ዉሀን ብቻ ቢጠቀም ምን ሊፈጠር ይችላል? ምንስ አዎንታዊ ለውጥ ይኖረዋል? የሚከተሉት ነጥቦችን ተመልከቷቸው… ጤናችንን በገዛ እጃችንን እንደምናጣ ይገባናል፡፡

1. የአእምሮ ቅልጥፍናን ያሻሽላል

“ፍሮነቲየርስ ኢን ሒዩማን ኒዩሮሳይንስ” የተባለዉ መጽሔት እንዳስነበበዉ ለ30 ቀን ለመጠጥነት ዉሀን ብቻ ብንጠቀም በእእምሮአችን እንቅስቃሴ ላይ ለዉጥ ማየት እንችላለን፡፡ አእምሮአችን በአግባቡ ለመስራት ብዙ የኦክስጅን መጠን ያስፈልገዋል፡፡ ይህንንም በብዛት የሚያገኘዉ ከምንጠጣዉ ዉሀ ዉስጥ ነዉ፡፡ ከ75-85 የሚሆነዉ የእእምሮአችን ክፍል በዉሀ የተሞላ ነዉ፡፡ ስለዚህ ዉሀን በመጠጣት አእምሮአችን በየጊዜዉ በቂ ሀይል የሚያገኝበትን መንገድ መፍጠር አለብን፡፡

2. ክብደትን በቀላሉ ለመቀነስ ያስችላል፡፡

ከሌሎች መጠጦች በተቃራኒ ዉሀን መጠጣት ዉፍረትን ይከላከላል፤ ይህን ደግሞ ሁላችንም ምስክር ልንሆን እንችላለን፡፡ “ሔልዝ ፊትነስ ሪቮሉሽን” እንደገለፀዉ ከእንቅልፍ እንደነቃን አንድ ብርጭቆ ዉሀ መጠጣት የምግብ መፈጨትን በ24% ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም የስብ መቃጠል ሒደትን የሚያዉኩ መርዛማ ነገሮችን እንዲወገዱ ያደርጋል፡፡ የምግብ ፍላጎታችንንም ይቀንሳል፡፡

3. አጥንትን ጤናማ ያደርጋል

ብዙ በተንቀሳቀስን ቁጥር መገጣጠሚያዎቻችን በብዙ ይጎዳሉ፡፡ ዉሀ ለስላሳ አጥንቶቻችንን እና ሌሎች ህዋሳቶቻችንን በማደስ መገጣጠሚያዎቻችን ስራቸዉን በብቃት እንዲሰሩና አጥንቶቻችን ጠንካራ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህም በቀላሉ መተጣጠፍን ሲያስችል የመተጣጠፊያ ቦታዎች ህመምንም በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ በአጠቃላይ ዉሀ ለሰዉ ልጆች የህይወትና የጤና ምንጭ ነዉ፡፡ የምንወዳቸዉ ሌሎች ብዙ የመጠጥ አይነቶች ከጥቅማቸዉ ጉዳታቸዉ ይበልጣል፡፡ እንደዉም ሰዉነታችን ብዙ ዉሀ እንዲያጣም ያስገድዱታል፡፡ ስለዚህ ብዙን ጊዜና በተገኘዉ አጋጣሚ የጤና ባለሙያዎች ብዙ ዉሀ እንድንጠጣና ሌሎች የመጠጥ አይነቶችን እንድንቀንስ የመምከራቸዉ ጉዳይ የሚያስደንቅ አይደለም፡፡

4. እድሜን ያረዝማል

በቂ ዉሀ በመጠጣት የቆዳችንን የዉስጠኛዉን ክፍል ማለስለስ ይገባል፡፡ ይህን በማድረግም የእርጅና ሂደትን ማዘግየት፣ ቆዳን ማደስ እንዲሁም የጡንቻዎቻችንን ብቃት መጨመር ይቻላል፡፡

5. በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል

በቂ የዉሀ መጠን መጠጣት ጉበትና ኩላሊት ጤናማ እንዲሆኑ ይረዳል፡፡ ይህም በደም ዉስጥ ያለዉን መርዛማ ነገሮች በብቃት እንዲያፀዱ ያደርጋቸዋል፡፡ በተጨማሪም በየቀኑ በቂ ዉሀ መጠጣት በሽታ የመከላከል ስርአትን ያጠነክራል፣ የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠር ያደርጋል፤ እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ የጤና እክሎችን ይከላከላል፡፡

6. ጤናማ ልብ ይኖረናል

በየቀኑ የምንጠጣዉ ዉሀ ደማችን እንዲቀጥን በማድረግ ቀልጣፋ የደም ዝውውር እንዲፈጠር ያደርጋል፤ ይህም የደም ግፊትንና ጥሰትን ይቀንሳል፡፡ የአሜሪካዉ የ”ኤፒዲሞሎጂ” መጽሔት የስድስት አመት ጥናት መሰረት አድርጎ እንደዘገበዉ ከሆነ በቀን ቢያንስ አንድ ብርጭቆ ዉሀ የሚጠጡ ሰዎች ልብና ልብ ነክ ለሆኑ በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸዉን በ41% ይቀንሳል፡፡

7. ይሄንን ስንቶቻችን እናውቅ ነበር? ላላወቀ እናሰውቅ፣ ሼር በማድረግ.....................

Posted on 01-31-18, 08:45 am


Karma: 100
Posts: 341/365
Since: 07-14-15

Last post: 518 days
Last view: 41 days
Enamesegenalen Meluye!
Pages: 1