ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing ልጅነት. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 01-26-18, 07:43 am


Karma: 100
Posts: 574/769
Since: 03-20-17

Last post: 409 days
Last view: 409 days
ኑ እንጨማለቅ
#የልጅነት_ትዝታዎች_ከኮመንት_ላይ_ የተሰበሰበ
:
☞ ልጅ እያለው ጫት የሚቅም ተስፋ የቆረጠ ስው ይመስለኝ ነበር..
:
☞ ልጅ እያለሁ በሬድዮ ሲናገሩ ሬድዮኑ ውስጥ ገብተውይመስለኝ ነበር
ለመግባት ሞክሬለው ቦታው ስጠይቃቸውከኃላ ብለውኝ .,,.....
:
☞ ልጅ እያለው ወፍ ያራችበት ሰው
ሳንቲም ያገኛል ስባልወፍ እንድታራብኝ እፈልግ ነበር::
:
☞ የመኪና ታርጋ ቁጥር የመኪናው ዋጋ ይመስለኝ ነበር ልክእንደ አንበሣ
ጫማ ተለጥፎበት ሣይ::
:
☞ የቢራቢሮ ክንፍ ቀለም ከተቀባን
ሳንቲም ከመሬት ይገኛልስለሚባል ቢራቢሮ አሳደን እንይዝ ነበር ።
:
☞ ልጅ እያለው ትምህርት አለፈ ሲባል ጉርጓድ ዘሎ ማለፍ ይመሥለኝ
ነበር::
:
☞ መብራት ሲጠፋ የመኪና መብራትም የሚጠፋ ይመስለኝ ነበር።
:
:
☞ በመኪና ስንሄድ መኪናው እራሱ
መንገድ የሚመራን ይመስለኝ ነበር።
:
☞ ወክ እንብላ ሲሉ ታላላቆቸ የሆነሚበላ ያለ ይመስለኝ ነበር።
:
☞ ልጅ እያለሁ ሲጋራ አጫሽ የተማረ
ሰው ይመስለኝ ነበ ለካስ ነገሩ ወዲህ ነው::
:
☞ ድሮ ልጅ እያለሁ ሰባራ ባቡር ሲባል የተሰበረ ባቡር ያለ ይመስለኝ
ነበር:እናትና አባቴ 'እናትና አባት' እንጂ ባል እና ሚስት አይመስሉኝም ነበር።
.
☞ እኔ ደሞ የመንግሥቱ ስሙ የተሰጠው መንግስት ሥለሆነ ይመስለኝ
ነበር
:
☞ ት/ቤት ተንጠልጥሎ አለፈ ሲባል
በገመድ ይመስለኝ ነበር፡፡
.
☞ "በጥቁር ቴሌቪዥንኣችን ፊት ላይ
የሚሸፈነው ሶስትመአዘን ዳንቴል ትግርኛ ዜና አንባቢውን "ሙዲአሊ‘ን"
እንዳይበርደው ይመስለኝ ነበር"
:
☞ አባቴ በቀበቶ ሰለሚገርፈኝ ማታ ሊተኛ ቀበቶውን ሲፈታእናቴን ሊገርፋት
የመስለኝ ነበር ።
:
☞ እማዬ "ሰላም ያዋልከን ሰላም
አሳድረን! ?…"ብላ ወደመኝታችን ልንገባ መብራት ስታጠፋ፤የምድርን ሁላ
መብራት ያጠፋችው ይመስለኝ ነበር…
:
☞ ከአባቴ በላይ የሚፈራና እውቀት
ያለውሰው ያለ አይመስለኝም ነበር።
Pages: 1