ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Singles & Dating . | 2 guests | 1 bot
Pages: 1
Posted on 01-26-18, 07:37 am


Karma: 100
Posts: 572/746
Since: 03-20-17

Last post: 2 hours
Last view: 2 hours
**ሁለት የተጣሉ ፍቅረኞች ተረብ**
…………………………………………………
ፍቅር ፍቅር ስልሽ ብር ብር እያልሺኝ
ፍቅርዬ አሁንስ ብርሌ መሰልሺኝ
ትልቅ ሆድ ነው እንጂ ጭንቅላት የለሽም
…………………………………………………
ባይገባህ ነው እንጂ ብርሌስ አንተ ነህ
ሰፊ ኪስ ነው እንጂ ሰፊ አይምሮ የለህ
…………………………………………………
ለህይወቴ ስንቅ ትሆኛለሽ ብዬ
ከልቤ ባስገባሽ ሞትኩኝ ተቃጥዬ
ወደ ላይ ሊለኝ ነው ውጪልኝ አንቺዬ
…………………………………………………
አንተ ሆነህ እንጂ ዛሬም አድሮ ቃሪያ
ከወጣው ቆየሁኝ ካንተ የዛገ ጣሪያ
አንተን ከምሆንህ የልብህ ወጌሻ
ባሳድግ ይሻላል ትንሽዬ ውሻ
…………………………………………………
ድሮስ መቼ ጠፋኝ ክብር አይወድልሽም
ለውሻ ነው እንጂ ለሰው አላለሽም
ከጊዜ በኋላ አሁን ተምሬያለው
ድሮም ከቁንጫ ቀጠሮ ተቃጥረው
አንዴም እፎይ ሳይሉ ሲዘሉ መኖር ነው
…………………………………………………ፓ!…ባንተ ቤት ይሄኔ አውርተህ ሞተሀል
ይሄን አይምሮህን ውሀ አርከፍክፍበት
ቶሎ ያድግልሀል
በል እንግዲህ ስማኝ……………
አውቄያለው እያልክ አፍህን አትክፈተው
ሁሉም እንዳይሸሹህ የበሰበሰውንአይምሮህን አይተው ።
Pages: 1