ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 01-23-18, 06:43 pm


Karma: 100
Posts: 567/741
Since: 03-20-17

Last post: 27 days
Last view: 19 days
ለቤት ተከራዮች ጠቃሚ ምክር
.
አከራዮችህ የቤት ኪራይ በየጊዜው ያላግባብ እየጨመሩብህ/ሽ/
ተቸግረሃል /ሻል/? ... እንግዲያውስ አንዳንድ ተሞክረው ጠቃሚነታቸው
የተረጋገጡ
ምክሮች እንደሚከተለው ይቀርባል:-
.
1ኛ ~ ስጋ ነክ ምግቦች አከራዮችህ እንዳይሸታቸው በተቻለህ መጠን ቤቱ
ውስጥ አለመስራት፡፡ ቢቻል ዘመድ ቤት ተሰርቶ ይምጣ፡፡ ሁሌ ስጋ ከበላህ
ሀብታም ነው ብለው ስለሚገምቱ ኪራይ ይጨምሩብሃል !
.
2ኛ ~ ነጭ ስኒከር ጫማ በተቻለህ መጠን አለማድረግ፡፡ የግድ ከሆነ
በፌስታል ይዘህ ውጣ !
.
3ኛ ~ ጋላክሲ ሞባይል ካለህ በጅ አንከርፍፎ አለመሄድ፡፡ ካልሆነ በተላላጠ
ከቨር ደበቅ ማድረግ !
.
4ኛ ~ ስትገባና ስትወጣ አንገትህን 45 ዲግሪ ዘመም አድርገህ ... ኑሮ
የከበደው ከዛሬ ነገ እራሱን የሚያጠፋ ሰው መምሰል !
.
5ኛ ~ እነሱ የሚጾሙ ከሆነ ስለሚሸት አርብ እና እሮብ እንቁላል
አለመጥበስ፡፡ ቀቅለህ ከበላህ በኃላ ቅርፊቱን እንዳያዩት ወደ
ጓሮ ወስደህ መቅበር !
.
6ኛ ~ አዲስ የቤት ዕቃና ልብስ ስትገዛ ማሸጊያዎቹን አዛው ጥሎ
ማምጣት ይመረጣል፡፡
.
7ኛ ~ ቤትህ ውስጥ ከልክ በላይ አለመሳቅ .... የግድ ከሆነ ግን ትራስ
ተጠቀም !
.
8ኛ ~ ገርል ፍሬንድህ ስትመጣ ግቢውን የሚያውድ ሽቶ እንዳትቀባ
መምከር !
.
9ኛ ~ ውሃ ስትቀዳ ባልዲውን አታስጩህ፡፡ አንድ በርሜል የቀዳህ
ይመስላቸዋልና፡፡
.
10ኛ ~ የእንግሊዝኛ ሙዚቃ በተቻለ መጠን አለመክፍት፡፡ የሚወዱትን
የሙዚቃ አይነት በረንዳቸው ላይ ማታ ማታ እየቆምክ ማጥናት፡፡ ከዚያ
ቅዳሜ እና እሁድ አንድ ላንተ ! ... አንድ ለነሱ እያረክ እንደ ዲጄ ማጫወት፡፡
አሁን ብታስጮህም ግድየለም !
.
11ኛ ~ ፊልድ የምትወጣ ከሆነ ከቻልክ ከሰል ካልቻልክ ጦስኝ
ነገር ማምጣት !
.
12ኛ ~ አንዳንዴ ባትፈልግም ጓደኞችህ ቤት ማደር፡፡ አለበለዚያ 'ሌላ
መሄጃም የለው' እንዴ ይሉሃል፡፡
.
13ኛ ~ የቤቱን ባለቤቶች ሴትዬዋን አሮጊት ካልሆኑ በቀር ፈጽሞ አንቱ
አለማለት፡፡ የሰውየው ችግር የለውም !
.
ይህን ሁሉ አድርገህ ግን ያላግባብ ኪራይ እየጨመሩብህ ካስቸገሩህ ...
አማራጭ የለህምና በቃ ሌላ ቤት ፈልግ፡፡ ፈጽሞ አትለማመጥ ! ...
ምክንያቱም አንድ ቀን ማታ ደክሞህ ከስራ ስትመጣ ... ሴትዬዋና ትልቋ
ልጃቸው በረንዳ ላይ ይጠብቁህና "ስማ ቤቱን አድሰነው ... ዱባይ
የምትኖር አንድ እህታችን ስለምትመጣ ለሷ መኖሪያ ልንሰጣት አሰብናል"
ብለው አንተን አስወጥተውህ ... ብር ጨምረው ቤቱን ለሌላ ሰው
ማከራየታቸው አይቀርም !!
Pages: 1