ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Ethiopian News & Events አዲስ ዜና. | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 01-20-18, 07:46 pm


Karma: 90
Posts: 727/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
እግር ኳሳችን ደረጃዎችን አሻሻለ ምንድነው ነገሩ

በፊፋ የወሩ የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ 6 ደራጃዎችን በማሻሻል ከዓለም 137ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 42ኛ ሆናለች
ከአፍሪካ ቱኒዚያ(23) ቀዳሚውን ስፍራ ስትይዝ ሴኔጋል(24) ትከተላታላች፡፡
ግብጽ(30)፤ ሞሮኮ(39)፤ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ(43)፤ቡርኪና ፋሶ(44)፤ ካሜሮን(45)፤ ጋና(50)፤ ናይጄሪያ(51) አልጄሪያ(57) ኮትዲቯር(61) ከሶስተኛ እስከ 12ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
ከዓለም ደግሞ 1ኛ እስከ 14ኛ ያሉት ደረጃዎች ምንም ለውጥ ያልታየባቸው ሲሆን ጀርመን፤ ብራዚል፤ፖርቱጋል፤ አርጄንቲና፤ቤልጂየም፤ ስፔይን፤ፖላንድ፤ ስዊዘርላንድ፤ ፈረንሳይና ቺሊ ከ1ኛ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
በወሩ ደረጃ ሰንጠረዥ ከፍተኛ ማሻሻልን ያሳዩት ሱዳን በ12 ደረጃዎች፤ ኤልሳልቫዶር በ10 ደረጃዎች እና ትሪኒዳድ ኤንድ ቶቤጎ በ7 ደረጃዎች ቀዳሚ መሆን ችለዋል፡፡
ከፍተኛ የደረጃ ማሽቆልቆል ያሳዩት ደግሞ ሱሪናሜ በ32 ደረጃዎች፤ ሃይቲ በ31 ደረጃዎች እንዲሁም የመን በ18 ደረጃዎች ተጠቃሽ ሆነዋል፡፡
ሶማሊያና ኤርትራን ጨምሮ ስድስት ሃገራት ደግሞ ዜሮ ነጥብ አግኝተው በፊደል ቅደም ተከተል ተበላልጠው እኩል 206ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

Pages: 1