ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 01-20-18, 08:00 am


Karma: 100
Posts: 565/741
Since: 03-20-17

Last post: 27 days
Last view: 19 days
"Chat Master" Mamush
አንዷ በውስጥ መስመር በተጣደፈ ስሜት 'ሰላምታ የለ' ፡ 'ምን ላይ ነህ' የለ (ያውም በዚች ከስቅታ ባነሰች ቅለት 'ሃይ' ብሎ መገላገል በሚቻልበት መንደር) ዝም ብላ
....ዘው!... ብላ ገብታ
"ቆይ ይች አገር ወዴት እየሄደች ነው!?" ... አለችኛ፡፡
እኔ፡- "ወዴት ብለሽ ነው የተሳፈርሽው?"
እሷ፡- "ቀልዴን አይደለም!...ግን ወዴት እየሄደች ነው!?"
እኔ፡- "ሆ! ለምን ሹፌሩን አትጠይቂም!?"
እሷ፡- " ለምን ሹፌር ፡ ተሳፋሪ ምናም እያልክ የወያላ ቀልድ ትቀልዳለህ!?"
እኔ፡- "የወያላ ቀልድ ብችል ምን እዚ ካንቺ ጋር አዳረቀኝ!!... ቀልዴን በስቲከር እያሳተምኩ ለመኪኖች ቸበችበው ነበር"
እሷ፡- "እንደ አንተ አይነቱ የወንድ አራስ እኮ ነው ህዝቡን ያስበላው"
እኔ:- "ቆይ አገራችን ምን ሆነች?"
እሷ፡- "ግርግሩን አልሰማሁም ለማለት ነው?"
እኔ ፡- "እእእ እሱ ነው እንዴ, እኛም እኮ መንግስት ልንገለብጥ ብለን ካርቦን አጣን"
እሷ ፡- "አሹፈህ ሞተሀል"
እኔ :- "የምሬን እኮ ነው በAndroid downloder ከስልጣን ልናወርደው ነው"
እሷ :- " እግዚአብሔር ይማርህ! ስለአገር ሲያወሩህ እንኳ ለዛ የሌለህ ቀዌ ነህ!"
እኔ፡- "እኔ ነኝ ወይስ በዚህች በህገወጥ መንገድ ወዴት እንደምትሄድ በጠፋት አገር ተሳፍረሽ ' ይች አገር ወዴት እየሄደች ነው?' ብለሽ የምትጠይቂው አንቺ ነሽ ቀዌ!?"...ልላት ስል ቦልካኛለች፡፡
Pages: 1