ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 2 guests | 1 bot
Pages: 1
Posted on 01-20-18, 07:54 am


Karma: 100
Posts: 564/741
Since: 03-20-17

Last post: 27 days
Last view: 19 days
ልብ የሚነካ መሳጭ ታሪክ"
በቃሉ የ4ኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡በትምህርቱ ግን ደካማ ነው፡፡ አስተማሪው ክላስ ውስጥ በጣም ትጮህበታለች እንዲያሻሽል ትመክረዋለች አልፎ አልፎም ትቀጣዋለች ከባሰም ትረግመዋለች፡፡
በቄ ቤት ውስጥም ከእናቱም ጋር አይስማማም፡፡ አንድ ቀን እናቱ ት/ቤት ሄደው ለልጃው ክትትል እንዲያደርጉ ለመምህሯ ነግርው ተመለሱ፡፡ በቄ ግን ያ ው ነው፣ ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ

ከ25 አመት በኀላ መምህሯ የልብ ህመምተኛ ሆና ወደ ሆስፒታል ትሄዳለች፣ ከፊቷ የዋህ፣ ሳቂታና አስተዋይ የሆነ ዶክተር እያናገረት፣ ችግሯን እየጠየቃት ህመሟን ሲያቀልላት ይሰማታል፡፡ ማደንዘዣውን ሲወጋት ትኩር ብላ እያየችው እጇን እያወራጨች መናገር የምትፈልገው ነገር እንዳለ እየነገረችው በዛው አሸለበች፡፡


በቃሉ ዶክተር ሆኗል ብላችሁ ከጠበቃችሁ የህንድ እና የአማርኛ ፊልም አፍቃሪ እንደሆናችሁ አስባነናችሁ፡፡ ወይም Motivational trainings በጣም ወስዳችኀል ማለት ነው፡፡

መምህሯ ከዶክተሩ ኀላ በቃሉን የፅዳት ልብሱን ለብሶ ቬንትሌተር ሲያስተካክል ነው ያየችው፡፡
(እንዴት ነው ...ታሪኩ ልባችሁን አልፎ ጨጓራችሁን ነካችሁ)

ህይወት አክተሩ የማይሞትባት ፣ ሲፈለግ ከሰማይ ዱብ የሚባልባት መድረክ አይደለችም፡፡
"ጥረትህ ከዕድል መስመርህ ጋር ሲጋጠም ያኔ ስኬትህ እውን ይሆናል:: የአንተ ድርሻ እንደ ንብ ታታሪ ሆኖ መስራት ነው፡፡" የዕለቱ መልዕክታችን
Pages: 1