ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 01-19-18, 07:48 am


Karma: 100
Posts: 563/741
Since: 03-20-17

Last post: 26 days
Last view: 19 days
ጢርርር ጢርርር ስልኬ እየጮኸ ነው ሲስተር ነች ከ USA .......በዚህ ሰዐት ምን አስደወላት?ይሄ የፈረደበትን ሽሮ ላኩልኝ ልትል ነው ብዬ ተሳቀኩኝ፣ ባለፈው ጎረቤታችን እማማ ዘርፌ ውለታዋ አለብኝ ብለው አበጥረው አስነፍተው ማኛ የሆነ ነገር ልከውላት ነበር.....ወይስ ፕሮሰስህን ጨረስኩልህ ና ልትለኝ ነው ??ስልኩን አነሳሁት
እኔ፡- እንደ ዶላሩ ድምፅሽም እኮ ውድ ሆነ
እሷ፡- አጎት አረኩህ፣ ለልጄ ስም አውጣለት እስኪ (ሰላምታ ድሮ ቀረ ሰላም የቺክ እና የባስ ስም ከሆነ በኀላ)
እኔ፡- እንዴ እንደጫንሽ እኮ አልነገርሽኝም Anyways እንኳን ማርያም ማረችሽ
እሷ፡- አሁን ስም አውጣለት አገትተኝ
እኔ፡- እሺ "አዳም" በይው
እሷ፡- እንዴ የድሮ ስምማ አላወጣም ምድር ሲፈጠር የነበረ ስም እኮ ነው
እኔ፡- "ሽብሩ" በይው (ዘመኑ የአሸባሪዎች ነውና)
እሷ፡- ልጄንማ ቴረሪስት(Terrorist) ብዬ አልሰይምም
እኔ፡- Ok "ሳራ" (የምወዳት ጓደኛዬ ስም)
እሷ፡- ወንድ እኮ ነው የወለድኩት አሞሀል እንዴ
እኔ፡- "ሽናባቸው" (ከሳራ ጋር ተቀራራቢ ስለሆነ)
እሷ፡-ውይ እስኪ ከስነተዋልዶ እና ከመራቢያ አካላት የራቀ ስም አውጣ ከሀይማኖት ና ከፓለቲካ ጋርም አታገናኘው
እኔ፡- እሺ "በቃሉ" በይው
እሷ፡- ሰው "በፅሁፉ" እንኳን በማይታመንበት ሰዐት እንዴት "በቃሉ"ይባላል??
ከብዙ ጭቅጭቅ በኀላ "መታደል" አልነው፡፡


ትንሽ ቆይታ ድጋሚ ስደውልልኝ የሆስፒታሉ ስም መዝጋቢዎችን yahoo አልያም Gmail ነው የላካቸው መሰለኝ "መታደል8767" ብለው እንዳፀደቁት ነገረችኝ፡፡
Pages: 1