ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 2 guests | 1 bot
Pages: 1
Posted on 01-19-18, 07:43 am


Karma: 100
Posts: 562/741
Since: 03-20-17

Last post: 27 days
Last view: 19 days
አንዲት ወፍራም ሴት ባስ ላይ ትሳፈራለች።አንዱ ተሳፋሪ "ይሄ ባስ
የዝሆኖች መሆኑን አላወኩም ነበር" አለ።ነገሩ የገባት ወፍራሟ ሴትም
"አይዞህ ባሱ እንደ ኑህ መርከብ ነው።ዝሆኖችም አህዮችም ይሳፈሩበታል "
ብላ አፉን አዘጋችው።
፠፠፠
②አንድ ወጣት ፀሐፊ ወደ ታዋቂ ደራሲ ጋ ይሄድና "አንድ መፅሐፍ አብረን
እንፃፍ "አለው ።ደራሲውም የንቄት ሳቅ ሳቀና "አህያና ፈረስ በአንድ ጋሪ
ሲስቡ አይተህ ታውቃለህ "አለ።ወጣቱ ፀሐፊ ምን አለው
መሠላችሁ ? "ምንም ያህል ብትንቀኝም ፈረስማ ብለህ አትሰድበኝም!"
★★★
③ሴትዮዋ አህዮች ይዛ በሆኑ ወጣቶች ዘንድ አለፈች።ወጣቶቹም "አሰላሙ
አለይኩም ያህዮች እናት "አሏት እየተሳሳቁ።ሴትዮዋም ፈገግ አለችና
"ወአለይኩሙሰላም ልጆቼ "!
∅∅∅
④የሆነ ንጉስ በግ አሳረደና አንዱን ገጠሬ ይጋብዘዋል።ታዲያ ገጠሬው
አበላሉ አይጣል ነው።ንጉሱም በመገረም "ምነው እናቱ የወጋችህ ይመስል
እንዲህ የምትበላው ?!"አለው ።ገጠሬውም "አንተ ደግሞ ስታዝንለት ላየህ
እናቱ ያጠባችህ ነው የምትመስለው" ብሎት እርፍ።
Pages: 1