ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Music. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 01-14-18, 08:16 pm


Karma: 90
Posts: 712/887
Since: 02-29-16

Last post: 339 days
Last view: 339 days
የጠፋችው_ባለቅኔ_ድምፃዊ_እጅጋየሁ_ሽባባው_(ጂጂ)

በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ አቻ ያልተገኜላት ድንቅ የግጥም፣ የዜማ ደራሲና ድምፃዊ እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) ናት ብል ማጋነን አይሆንብኝም። ይቺ አርቲስት ዝም ብላ ሞትኩልህ ያዘኝ ልቀቀኝ እያለች አይደለም የምትዘፍነው፤ የኢትዮጵያ ታሪክን፣ ባህልንና ፍቅርን ነው የምታዜመው። ለምሳሌ ኢትዮጵያ፣ አድዋ፣ አባይ፣ እስከ መቼ፣ ካህኔ፣ ፍቅር እየራበኝ፣...... ድንቅ ብቃቷን ያሳየችበት ጥቂቶቿ ዜማዎቿ ናቸው። ሙዚቃዎቿ ከሀገር አቀፍ እስከ ሆሊ ውድ ፊልሞች ድረስ በማጀቢያነት ስራ ላይ ውለዋል። ከዚህ በተጨማሪ በአሜሪካ በCNN ቲቪ በተደጋጋሚ ቀርበዋል፤ ኢንተርቪው ተደርጋለች። በአጠቃላይ ቀደም ባለው ጊዜ በአጭር አመታት አምስት ካሴት በማውጣት ትልቅ የሙዚቃ ስጦታ ለሙዚቃ አድማጮች አበርክታለች።
ታዲያ ይቺ ድንቅ እንስት ሞገዴኛ አርቲስት አዳዲስ ስራዎችን ከመስራትና መድረክ ላይ ስራዎቿን ከማቅረብ ከራቀች ከ10 አመታት በላይ ሆኗታል፤ እንደው ምን ሆናብን ይሆን??? ፈጣሪ በመልካም ጤንነትና በሰላም ጠብቆ ዳግም ሌሎች ስራዎቿን ለሙዚቃ አድማጮቿና አድናቂዎቿ እንዲታቀርብ ልባዊ ምኞቴ ነው። ሰላም እንድትሆኑ ተመኘሁ ለእናንተም ለእሷም!!!!!Posted on 01-15-18, 12:14 am


Karma: 95
Posts: 732/852
Since: 07-22-15

Last post: 222 days
Last view: 138 days
Gg andegnchn
Pages: 1