ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing General Healthcare . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 01-09-18, 07:44 am


Karma: 100
Posts: 393/426
Since: 07-12-15

Last post: 339 days
Last view: 339 days
የጨጓራ በሽታን ለማስታገስ የሚጠቅሙ 3 የቤት ውስጥ ውህዶች

ሰሞኑ የበዓል ነው፡፡ አምሮት የሚቀሰቅሱ ቅባታማ እና በርበሬያማ ምግቦቻቻንን ባላየ ማለፍ የምንችልበት አቅም ያለን አይመስልም፡፡ ስለዚህ የልብ አድርሶ የመሸመበት ማደር ነው ብልን እጃችንን ሰብሰብ አድርገን የገባንበት ካለን እንግዲያውስ ለጨጓራችንም መላ እንፈላልግለት፡፡ እነዚህን በቤት ውስጥ ማዘጋጀት የሚቻሉትን ውህዶች በመጠቀም እርፍ ማለት እንችላለን፡፡

1- የድንች ጭማቂ

(ድንቹን በ ጁስ መፍጫ ከፈጨነው በኋላ ውሃውን በቀን አንዴ 3 ወይንም 4 የሾርባ ማንኪያ መጠጣት ፡፡ ህመማችን ባስ ካለ በ ቀን ሁለቴ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ይህ የጨጓራችንን የ ph መጠን የሚያረጋጋው ሲሆን የጋዝ ምርቱን እንዲቀንስ በማድረግም የማቃጠል ስሜትን ያጠፋል፡፡

2- የሩዝ ውሃ

(ሩዝ የተቀቀለበትን ውሃ ለተለያየ የህክምና ዓላማ መጠቀም አሁን አሁን ዓለማችን ላይ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ ጉዳይ እየሆነ መጥቷል፡፡ትንሽ ሩዝ በውሃ ከጣድን በኋላ ሩዙ እንደመብሰል ሊል ሲል የውሃው ቀለም ነጭ ይሆናል ያኔ ውሃውን አጥልሎ በመጠጣት የማቃጠልን ስሜት ማጥፋት ይቻላል፡፡ )

3- ማር

(2 የሾርባ ማኒኪያ ንፁህ ማርን ለብ ባለ ውሃ በጥበጥ አድርገን በመውሰድ ከፍተኛ የሆነ ጥቅም ልናገኝ እንችላለን፡፡ህመሙ ሊጀምረን አከባቢ ብናደርገውደግሞ የበለጠ ፍቱን እንደሆነ ይታመናል፡፡

Posted on 01-13-18, 07:23 am


Karma: 95
Posts: 718/852
Since: 07-22-15

Last post: 90 days
Last view: 6 days
Mealu gn cheguarashin yamshal endea? Degagemshat
Pages: 1