ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing ግጥሞች. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 01-09-18, 02:48 am


Karma: 90
Posts: 693/887
Since: 02-29-16

Last post: 339 days
Last view: 339 days
ዛሬም እፅፋለሁ

ሻማየን ለኩሼ….ናፍቆትሽን እየሞኩ
ጉልበቴን አጥፌ…ነገን እየናፈኩ
መምጫሽን …እያለምኩ….ነጭ ወረቀት ሙሉ ቃላት እየሰዋሁ
ነፍስና ስጋሽን በቃል እከተፍኩ…በደም ተዘፍቄ…በደም ተለውሼ…ወንጀለኛ ሆኜ
ቁጭ ብየ እንዳደርኩት
ዛሬም አደርጋለሁ፡፡
መስየሽ እየኖኩ
በከዋከብት ብርሃን
በውብ ፅጌሬዳ
በወይን ዘለላ…በጨረቃ ፀዳል…
የፍቅር አፍሮዳይት ብየ እንደሰየምኩሽ…ወኔ እየሞላ
ከውስጤ ሳያጥጥ ቃላት ሳይነጥፍብኝ…..በውዳሴ ዜማ…ያኔ እንደካብኩሽኝ
የመውደድሽን ልክ…የማፍቀርሽን ጣራ
አግዝፌ እያሳደኩ…በብዕር ቀለማት ስስልሽ እንዳደርኩ
ዛሬም አደርጋለሁ፡፡
ዛሬም እፅፋለሁ፡፡
ትላንት
የኔ መሆንሽን በነገርሽኝ ጊዜ
ያኔ እንደማደርገው
ብዕሬን የምጨምቅ…ቀለም የማሰስተፋው
ስለ አንች…እየከተብኩ….በቃላ­ት የማጌጥ…ቤቴን የምሰራው
በአይን እና ከንፈርሽ…በጥርስና ሳቅሽ
ለዘብ በተጠሩት…በቆሙት ጡቶችሽ
በዳሌሽ መሸንቀጥ…በሚያምረው ወገብሽ
በሎሚ ተረከዝ…ባማላዩ ባትሽ
በሆኔ እያሞፈ,ገስኩ…..እያልኩ­ እንዳልካብኩሽ
በጠላሽኝ ጊዜም …..ዛሬም እጽፋለሁ፡፡
እጽፋለሁ ለአንች
የበራውን ሻማ ጸዳሉን አጥፍቸ….በጠቆረ ፅልመት በኩራዝ ተክቼ
ብዕሬን ሰብሬ…በርሳስ እስላለሁ
የፍቅር ቃላትን ከውስጠቴ አጥፍቼ….ጥላቻ እጽፋለሁ፡፡
እፅፋለሁ
ውዳሴ የሌለው….ምርር ያለ ሃዘን…..የጥላቻ ጎጆ….በወረቀት ሜዳ
ዛሬም እስላለሁ፡፡
እፅፋለሁ፡፡
ቃላት እጥላለሁ፡፡
ትላንት የሆነውን…የውዳሴን ዜማ
ዛሬ ተገልበጦ ህይወቴ ተዛማ
በፍቅርሽ ቅያሪ….ጥላቻሽን ገዛሁ
በደልሽን አሰብኩ…መለየትሽን ለየሁ
ሩቅ መሄድሽን…መጥፋትሽን አወኩ
የተለከፍኩበት መፃፍ ሆኖ ምሴ
ለፍልፍ ለፍልፍ …ሲለኝ…ተናግር ተናገር ዛሬም እጽፋለሁ፡፡
በፍቅር ስለፍቅር
በጥላቻም ጊዜ…ልክፍት ስለሆነኝ
ቃላት አጎራለሁ
ዛሬም እጽፋለሁ
ትላንትና ላንች ዛሬ ደግሞ ለእኔ
ቃላት እፈጥራለሁ…ህይወት እስላለሁ…ዙረት እዞራለሁ
ነገ ሌላ ታሪክ…ደግሞ ሌላ ፅፈት…ደግሜ እፅፋለሁ፡፡

By:Asefafaw
Pages: 1