ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 6 guests | 5 bots
Pages: 1
Posted on 01-08-18, 07:16 am (rev. 1 by ጮሌው on 01-08-18, 07:18 am)


Karma: 100
Posts: 551/736
Since: 03-20-17

Last post: 28 days
Last view: 28 days
አንብበው ሲጨርሱ ሼር ማድረግ እንዳይሩሱ!! አስተያየት ካለ ኮመንት ሳጥን ውስጥ ጣል አድርጉ!

የስራ ማስታወቂያ!

የስራ መደቡ መጠሪያ፦ ለአዲስ አመት የምትሆን ምርጥ ሚስት

የስራ ቦታው፦አዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ ሊለዋወጥ የሚችል! ደሞዝ፦በስምምነት!

አመልካቾች በስራ (በትዳር) ዘመናቸው ሊኖራቸው የሚገቡ ባህሪያት

ሰርግ የሚሉትን ነገር የሆነ እብድ ሰውዬ ከእለታት አንድ ቀን የጀመረው እቃቃ ጨዋታ መሆኑን የተረዳችና አንጃ ግራንጃ ሳታበዛ እንደቅርጫት ኳስ ጥልቅ ብላ ለመግባት የተስማማች

የቤት እመቤት በሚባለው የደከመ የስራ ዘርፍ ተሰማርታ ቡና ስትቀቅል የማትውልና ውጪ ሰርታ ለመግባት እንዲሁም ራሷን በትምህርት ሆነ በመሰል ድርጊቶች የተሻለ ሰው ለማድረግ ቁርጠኝነቱ ያላት!

በፍጹም! እደግመዋለው በ..ፍ..ጹ..ም ቂቤ የሚባል ነገር ማትቀባ! ማታ ስትተኛም ፊቷን ቫዝሊን ማትለቀለቅ! ሮንድ እንደሚወጣ ሰው ወደ አልጋ ስትሄድ ጋንባሌ የሚያክል ካልሲ ታጥቃ ውብ እግሮቿን የማትሸፍን!

ቀጣሪው human hair ን ልክ እንደ human nose ወይም እንደ human teeth ስለሚቆጥር የሰው ጸጉር እናቷ ላይ ማታጠልቅና በተፈጥሮዋ ምትኮራ

ፒንክ ከለር ያለው ማንኛውም አይነት ነገር ማትጠቀም ቅንድቧን በገዛ እጇ ላጭታ ግንባሯ ላይ ቅንድብ ለመፍጠር እንደትራፊክ ስታሳምር የማትውል! እንዲሁም ከመጠን በላይ ሜካፕ ተለቅልቃ ወፍጮ ውስጥ እንደገባች ድመት አመድ በአመድ ሆና የማትመጣ!

ፈጣሪ በቸራት የተፈጥሮ ውበትም ማትሸማቀቅ በራሷ የምትተማመን!

*ህይወት ቀሚስ ከመግዛትና ጸጉር ከመስራት እንደሚያልፍ የተረዳች
*የሄለን በርሄን ዘፈን ማታዳምጥ
*ባል ቢደውልም ሆነ ባይደውል ግድ የሌላት!
*ባል ደክሞት ቤቱ ሲገባ ስለሽሮና በርበሬ እንዲሁም መሰል የኩሽናና የወጥ ቤት ቅመማ ቅመሞች እያወራች የማትደክም
*ከመሬት ተነስታ አሊያም ሰበብ ፈልጋ ማታለቅስ!
*አልጋ ውስጥ ስትገባ ከአልጋ ውጪ አለም እንደሌለ የምታስብ ብርድ ልብስ ከገለጠች በኋላ "ከብርድ ልብስ በላይም ሆነ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም" ብላ የምታምን
*"ልጅ ባልወልድስ?" በሚለው አማራጭ ሀሳብ ላይ ለመወያየት ፈቃደኛ የሆነች!
*ለሊት ተነስታ ማትበላ

ስመታትም ለበጎ ነው የምትል

ከላይ የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምትስማሙና መስፈርቶቹንም የምታሟላ አመልካቾች ዘወትር በስራ ሰአት፦

*የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት
*ያላገቡ ስለመሆኖት የተጻፈ የቀበሌ ማስረጃ
*ሁለት ጉርድና አንድ የቁም ፎቶ። (ከፎቶው ጀርባ የፎቶሾፕ እጅ እንደሌለበት ቢሆን ይመረጣል)
*ህጋዊ የልደት ሰርተፍኬት (የልደት ሰርተፍኬቱ ከሌለ በቃል የተደገፈ የልደት መረጃ)
*ከማይመለስ መቶ ብር ጋር ይዘው ቢቀርቡ ጨረታውን መሳተፍ እንደሚችሉ እናስታውቃለን

ማሳሰቢያ፦ቀጣሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ የቅጥር ስምምነቱን ሙሉ በሙሉም ሆነ
በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
የናዝሬት ቺኮችን አናስተናግድም !!!

Pages: 1