ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 2 guests | 3 bots
Pages: 1
Posted on 01-08-18, 07:03 am


Karma: 100
Posts: 549/736
Since: 03-20-17

Last post: 27 days
Last view: 27 days
ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ ፀጉር ቤት አንድ
ጀርመናዊ ቄስ ፀጉሩን ይስተካከል እና ሂሳብ ስንት እንደሆነ ፀጉር አስተካካዩን ይጠይቀዋል……
ፀጉር አስተካካዩም «ጌታዬ ለእርሶ አደረኩ ማለት ለጌታ
አደረኩ ማለት ስለሆነ አላስከፍሎትም… በፍፁም አልቀበሎትም» ብሎ ይሸኛቸዋል…
:
በነገታው ጠዋት ፀጉር አስተካካዩ
ወደ ሥራ ሲገባ ከበሩ ስር ከቄሱ የተላከ አጭር የምስጋና ፅሁፍ እና በርከት ያሉ የፀሎት መፀሃፎች እንደ ስጦታ ያገኛል……
:
በሌላ ቀን ደግሞ አንድ እንግሊዛዊ የፖሊስ መኮንን ፀጉሩን
ይከረከም እና ሂሳብ ስንት እንደሆነ ይጠየቃል……
ፀጉር አስተካካዩም ‹አንተ ህብረተሰቡን
የምታገለግል ፖሊስ ስለሆንክ አላስከፍልህም ለህብረተሰቡ
እንዳደርኩ ነው የምቆጥረው ስለዚህ ነፃ ነው» ብሎ
ይሸኘዋል……
:
በነገታው ጠዋትም ፀጉር አስተካካዩ ወደ ሥራ ሲገባ
ከበሩ ስር ከፖሊስ መኮንኑ የተላከ አጭር የምስጋና ፅሁፍ እና በርከት ያሉ የተለያዩ ስጦታዎችን ያገኛል……
:
በሌላ ጊዜ ደግሞ አንድ ሀበሻ ፀጉሩን ይስተካከል እና ሂሳብ ይጠይቃል ፀጉር አስተካካዩም… «ታላቁን የኦሎምፒክ ጀግና አበበ ቢቂላን እና ኃይሌ ገብረስላሴን ካፈራች ሀገር የመጣ ሀበሻን ማስከፈል ይከብዳል…… ለነሱ ክብር እንዳደረኩት ስለምቆጥረው ነፃ ነው» ብሎ ይሸኘዋል……
:
በነገታው ጠዋትም ፀጉር አስተካካዩ ወደ ሥራ
ሲመለስ………………… አስራ ሁለት ሀበሾች ፀጉራቸውን ለመስተካከል ወረፋ ይዘው ነበር
Posted on 01-13-18, 07:38 am


Karma: 95
Posts: 725/845
Since: 07-22-15

Last post: 31 days
Last view: 8 days
Hahahahah
Pages: 1