ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 5 guests
Pages: 1
Posted on 01-05-18, 08:21 am


Karma: 100
Posts: 545/736
Since: 03-20-17

Last post: 27 days
Last view: 27 days
አይ ማዘር.... ያስቃሉ እኮ
.
የቤቴ አከራይ እኮ ናቸው ከዚህ በፊት ውሀ እንደመጣች ልጠይቃቸው
ደወልኩላቸው
.
"ሄሎ ማዘር.....ውሀ መጣች እንዴ? ስላቸው
.
"አይ ልጄ....እንደው 7up እየጠጣን እንደሆነ ጠፍቶህ ነው አሉኝ?
.
እየተወዛገብኩ....."እንዴ! የምን 7up ነው ደሞ" አልኳቸው
.
"ስልህ......ውሀ በሰባት ቀን አንዴ እንደምትመጣ ጠፍቶህ ነው"? ብለውኝ
አነፈሩኝ
.
(የዛን ሰሞን ውሀ በሳምንት ነበር የምትመጣው) ላለፉት አራት ወራት ግን
በወር አንዴ መምጣት ጀምራ ነበር
.
ቤት ባልኖር እንኳ ማዘር ደውለው "ና. እንግዲህ....እንዳመልህ እነዛ
ኮዳዎችህን ሳይቀር ሙላቸው...."የወር አበባ መታለች" ይሉኛል
.
ምን ዋጋ አለው ውሀ ይህም አመሏ ከቀረ ዛሬ አንዱን ወር ጨርሳ
ሁለተኛውን አጋምሳለች
ታዲያ አሁን ማዘር የተሰጣ ነጠላቸውን ከውጭ እያስገቡ አየኋቸውና
.
"እንዴ ማዘር! የወር አበባ መጣች እንዴ ስላቸው ምን ቢሉኝ ጥሩ ነው...
.
.
"አሂሂሂ.....! ባክህ ሰዎቹ የውሀ ማጥሪያ መስሏቸው የወሊድ መቆጣጠሪያ
ክኒን ገንዳው ላይ ሳይሞጅሩ አይቀርም"
Pages: 1