ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 4 guests | 3 bots
Pages: 1
Posted on 01-05-18, 08:11 am


Karma: 100
Posts: 542/738
Since: 03-20-17

Last post: 2 days
Last view: 2 days
ሀፒ በርዝደይ
የ35 አመት የልደት ቀኔ በመሆኑ ያን ቀን ከእንቅልፌ ስነሳ ደስ ደስ እያለኝ
ነበር፡፡ ግን ምን ያደርጋል ቁርስ ላይ ባለቤቴ" ሀፒ በርዝደይ"! ትለኛለች ብዬ
ስጠብቅ ጭራሽ አኩርፋለች፡፡ ልጆቼም እንደዛው፡፡
ስራ ስገባ ግን ፀሀፊዬ ሮዛ " ሀፒ በርዝደይ!" ብላ ፖስትካርድና ጥቂት
ቸኮሌቶች ሰጠችኝ፡፡ አሁን በመጠኑ ጥሩ ስሜት ስለተሰማኝ ስራዬን
ተያያዝኩት ፡፡
ምሳ ላይ ፀሀፊዬ መጥታ "ዛሬ የልደት ቀንህ ስለሆነ ለምን ምሳ አብረን
አንበላም ?" በማለት ጠየቀችኝ ፡፡
እኔም እሺ ብያት እሷ ወደምታውቀው ሬስቶራንት ተያይዘን ሄድን፡፡ ምሳው
ግሩም ነበር፡፡
ከምሳ በኃላ ፀሀፊዬ "ዛሬ የልደት ቀንህ ነው፡፡ ቀኑ ደግሞ ደስ ይላል፡፡ ታዲያ
ለምን እኔ አፓርትመንት ሄደን አናከብርም ?" ስትል ጠየቀችኝ ፡፡
እኔም በባለቤቴና ልጆቼ ተናድጄ ስለነበር ምንም ሳላንገራግር እሺ አልኳት፡፡
አፓርትመንቷ ሁለተኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን ያምራል፡፡ ሳሎን የሚጠጣ
ነገር ቀድታልኝ " መኝታ ቤቱን አስተካክዬ መጣሁ " ብላኝ ወደ ውስጥ ገባች
፡፡
እኔም የወሲብ ፍላጎቴ አለቅጥ ንሮ በጥድፊያ ልብሴን አወላልቄ
መለመላዬን ሆኜ ፀሀፊዬን መጠባበቅ ያዝኩ ፡፡
ወዲያው ግን ፈፅሞ ያልጠበኩት ሆነ፡፡ ከውስጥ በኩል ባለቤቴ ልጆቼና
ጥቂት ጓደኞቼ " ሀፒ በርዝደይ ቱ ዩ!..."እያሉ እየዘመሩ ወደ ሳሎን መጡ፡፡
Pages: 1