ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 5 guests
Pages: 1
Posted on 01-04-18, 06:27 am


Karma: 100
Posts: 541/736
Since: 03-20-17

Last post: 27 days
Last view: 27 days
በቀደም በከተማችን ከሚገኙት ባሮች ውስጥ ባንዱ ከወዳጆቼ
ጋር
እየተዝናናሁ ቆየሁና ወደ መጸዳጃ ቤቱ አመራሁ፡፡ መፀዳጃ
ቤቱ
አጠገብ ላጠገብ በወፍራም ችፑድ የተለዩ 2 መቀመጫ
ያላቸው
ሽንት ቤቶችን ይዟል፡፡ እኔ ስደርስ በግራ በኩል ያለው ተይዞ
ስለነበር በቀኝ በኩል ያለው ላይ ዘው ብዬ ገብቼ ጉዳዬን
ጀመርኩ፡፡
ትንሽ ቆየት ብሎ ከችፑዱ ጀርባ አንድ ጎርናና ድምፅ “እሺ
ሰላም
ነው?” የሚል ጥያቄ አዘል ሰላምታ አቀረበልኝ፡፡ ድምፁን
የማላቀው መሆኑና መፀዳጃ ቤት ውስጥ ሳንተያይ እንኳን ወሬ
ለመጀመር መፈለጉ ግራ እያገባኝ ፤ ዝም ከማለት ይሻላል
በማለት
ብቻ “አለሁ ይመስገነው” ብዬ መለስኩለት፡፡
ጎረቤቴ አለቀቀኝም “ምን እየሰራህ ነው በናትህ?”
ሆሆ!! ስንት አይነት ሰው አለ ባካችሁ? በጣም እያናደደኝ “ያው
እንዳንተው ሽንት ቤት ተጎልቼ አይደል እንዴ ያለሁት፤ ምን
እየሰራሁ ይመስልሃል? ብዬ በቁጣ አምባረኩበት፡፡
እሱ ግን ቁጣዬን ከቁብ ሳይቆጥረው ጭራሽ “እንዴት ነው
አንተጋ
ልምጣ እንዴ?” አለኝ፡፡
እየመጣሽ ተኚ !! ምኑ ብሽቅ ነው ዛሬ ያጋጠመኝ እያልኩ
“ሰውዬ
አሁን ስራ ይዣለሁ አትጨቅጭቀኝ!!” ብዬ በድጋሚ
ተቆጣሁ፡፡
ወድያው የጎረቤቴ ድምፅ እንደመሰላቸት ብሎ “ኤጭ… ባክህ
ትንሽ ቆይቼ ልደውልልህ አንድ እብድ ካጠገቤ ቁጭ ብሎ
የምጠይቅህን ሁላ እየመለሰ ነው” ሲል ሰማሁት፡፡
ማካፈል ደግ ነው SHARE with your friends
Pages: 1