ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Government. | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 01-02-18, 09:33 pm


Karma: 90
Posts: 674/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
በመቶኛው አመት መጀመሪያ ላይ ከነበሩት የዘመነ መሣፍንት ተዋንያን አንዱ የደንቢያው ገዥ ደጃች ማሩ የካሣ ሃይሉ (የሇላው አፄ ቴዎድሮሥ) ዘመድ ሲሆን፣ ቇራን ጨምሮ በየቦታው ተበታትነው የሚገኙት ግዛቶች በጥቅል "የማሩ ቀመስ" ተብለው ይታወቁ ነበር። ደጃች ማሩ በ፲፰፻፳ (1820) በ"ኮሶ በር ጦርነት" ሢወድቅ ግዛቱ ወደ ደጃች ክንፉ ተላለፈ። በጎንደር የተወለደውና አንዳንዴ ካሣ ማሩ እየተባለ ይጠራ የነበረው ካሣ ኃይሉም ወደ ቇራ የሄደው ከዚሁ ከኮሶ በር ጦርነት በሇላ ነው። ካሣ ቇራ ውሥጥ በደጃች ክንፉ ቤት አደገ። በዚህም ጊዜ ግብፆች ከሡዳን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ለማሥፋፋት የሚያደርጉት ጥረት በብርቱ ይፋለሙ ከነበሩት መሣፍንት አንዱ ደጃች ክንፉ ነበር። በ፩፰፪፱ (1829) "ወድከልተቡ" በተባለ ሥፍራ በግብፅ ጦር ላይ ትልቅ ድል በመጎናፀፍም በኢትዮጵያውያን ዘንድ ስመ ጥር ሆኖ ነበር። የአባቱ ልጅ ለሆነው ለካሣ ግን ብዙም ፍቅር አያሣየውም ነበር።


አፄ ቴዎድሮስ

ክንፉ "የማሩ ቀመሥ"ን ለልጆቹ ለማውረሥ ለነበረው ፅኑ ፍላጎት ካሣን እንቅፋት ሆኖ ሥላየው የሚመለከተው በክፉ አይኑ ነበር። የማታ ማታ ግን ያ ሁሉ ልፋትና ጠላትነት ከንቱ ሆነ። ክንፉ እ.ኤ.አ. በ1839 ሲሞት "የማሩ ቀመሥ" ለክንፉ ልጆችም ሆነ ለካሣ ሣይሆን የራሥ ዓሊ እናት እቴጌ መነን ወረሠችው። ያኔ ነው ካሣም በሥርአት ያጣውን ግዛት በጉልበቱ ለማግኘት የሽፍትነትን ጎዳና የመረጠው።

ከጥቅት ጊዜ በሇላ ሌሎች ያኮረፉ ባለሟሎችንና ተራ ቀማኞችን እየመራ በቇራ በረሃ ጀመረ። ከሁሉም በላይ ካሣ በሽፍትነት ዘመኑ ነው ከግብፆች ጋር መጋጨት የጀመረው። በህይወቱ ሽንፈትን ያላወቀው ካሣ የመጀመሪያውንና የመጨረሻውን ማለት ይቻላል ወታደራዊ ሽንፈት የቀመሠው በ፲፰፻፵ (1840) ደበራቅ በምትባል ሥፍራ ላይ ነው። ጭፍን ድፍረት እንጂ የጦር ሥልት ያልታደለው የካሣ ሠራዊት በግብፅ መድፍ እንደ ጭዳ ታረደ። ካሣም ለካ ይሄም አለ ብሎ የወደፊት አቅታጫውን ለማሠላሠል ተገደደ። ሠልፍና መድፍን ያልያዘ ሠራውት የድል ተሥፋው የመነመነ መሆኑን ተረድቶ ሁለቱንም በጁ ማድረግ የእድሜ ልክ ጥረቱ ሆነ።


የአፄ ቴዎድሮስ ጦር

መጀመሪያ በግብፆች በሇላ ደግሞ በልብ ወዳጁ በእንግሊዛዊው ጆን ቤል (በኢትዮጵያዊ አጠራሩ ሊቀ መኯሥ ዮሃንሥ) አማካይነት ሠልፍና የውጊያ ሥልት ማሥተማር ጀመረ። ካሣ ለመድፍ ያለው አክብሮትም ደባርቅ ሜዳ ላይ ተረግዞ "ሴባስቶፖል" ብሎ የጠራው መድፍ በጋፋት ፋብሪካ ሢሠራ ታላቅ ልደቱን አገኘ። ዳሩ ግን ያ ቴወድሮሥ የተመካበት መድፍ፣ ያ ከደብረ ታቦር እሥከ መቅደላ አፋፍ በሥንት አሣር ተጎትቶ የተወሠደው መድፍ በእንግሊዞች ላይ ሣይሆን አበሻ መሃል ፈነዳ። ቴወድሮስም የህይወቱን ከንቱነት፣ የህልሙን ቅዘት በዚሁ ተረዳ።

የካሣ ሥምና ዝና በቇራ አካባቢ እየገነነ ሢሄድ ባለ ሥልጣኖቹን ራሥ ዓሊንና እናቱን እቴጌ መነንን ማሣሣብ ጀመረ። ከሃይል ዘዴ ይሻላል ብለውም በጦር ያገኘውን የቇራን ግዛት መረቁለት። በጋብቻ ለማሠርም የዓሊን ልጅ ተዋበችን ዳሩለት። ካሣ ለተዋበች ያለው ፍቅር ቇሚ የሆነውን ያህል ከአባቷና ከእናቷ ጋር ያደረገው እርቅ ግን ውሎ አላደረም። ዜና መዋዕል ፀሃፊው እንደሚተርክልን በየጁ ቤተ መንግሥት በደልና ንቀት ቢበዛበት ካሣ እንደገና የሽፍትነት ኑሮውን ቀጠለ። ዓሊና መነንም ካሣን ለማንበርከክ ጦር መላክ ያዙ። የተላከው ሁሉ ግን የሽንፈት ፅዋን እየቀመሠ መመለሥ ሆነ። ከሁሉም ተረት ሆኖ የቀረው "ይህን የኮሶ ሻጭ ልጅ አንጠልጥየ አመጣለሁ" ብሎ የፎከረውና ተሸንፎና ተማርኮ የፉከራ ቃሉን በመራራ ኮሶ እንዲውጥ የተገደደው ደጃች ወንድይራድ ነበር። ምርኮ ግን ለንግሥቲቱም ለመነንም አልቀረላትም። ጦሯ በካሣ ጦር ተበትኖ ንግሥቲቱም ለጥቂት ቀናት የካሣ ምርኮኛ ሆና ነበር።

እነዚህ የመጀመሪያ የካሣ ድሎች ሇላ በዘመነ መሣፍንት አውራዎች ላይ የተጎናፀፋቸውን ድሎች የሚያበሥሩ ነበሩ። የካሣን የጦር ጥበብ ባጎሉት በነዚህ ድሎች አማካይነትም የዘመነ መሣፍንት መሪ ተዋንያን በሚያሥገርም ፍጥነት አንድ በአንድ ድል ሆኑ። መጀመሪያ ጉር አምባ ላይ፣ ህዳር(19) ፲፰፻፵፭ (1845) የራሥ ዓሊ ታዛዥ የነበረው የጎጃሙ ድጃች ጎሹ ወደቀ። ይህ ጦርነት ከጎንደር ብዙም ባልራቀ ሥፍራ ላይ መደረጉ ካሣ ከመከላከል ወደ ማጥቃት መሸጋገሩን የመጨረሻ ኢላማውን የነገሥታቱ መዲና መሆኑን አመለከተ። ከአንድ አምሥት ወር በሇላ፣ በሚያዝያ ፭ ቀን ደግሞ ካሣ አራት የራሥ ዓሊን ደጃዝማች "ጎርጎራ ብችኝ" በተባለ ጦር ሜዳ ላይ አሸነፈ፤ ከነዚህ ሁለቱ እዚያው ጦር ሜዳው ላይ ሞቱ። ራሥ ዓሊ እንዲህ እርቃኑን ከቀረ በሇላ የካሣን ጦር መመከት አልቻለም። በሰኔ ፳፮ (26) ቀን አይሻ ላይ ጦሩ ተበትኖ እሡም ወደ እናት ሆድ የመመለሥ ያህል ወደ የጁ ግዛት ማምለጥ ነበረት።

ከዚህ በሇላ በካሣና በዙፋኑ መካከል የነበረው መሠናክል አንድ ብቻ ነበር፣ የሠሜኑ ደጃች ውቤ። እሡም በየካቲት ፫፣ ፲፰፻፵፯ (1847) "ደረሥጌ" ላይ የሽንፈት ጽዋ ቀመሠ። ካሣ ለመንገሥ ወደ ጎንደር መመለሥ አለብኝ ብሎ አላመነም። እዚያው ደረስጌ ላይ ውቤ ባሣነፀው የማርያም ቤተ ክርሥትያን ከግብፅ ባሥመጣው ጳጳስ በአቡነ ሰላማ አማካይነት "ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ" ተባለ።


አፄ ቴዎድሮስ "ንጉሠ ነገስት ዘኢትዮጵያ" ተብለው ደረስጌ ማርያም ቤተክርስትያን ውስጥ ዘውድ ሲጭኑ


ደረስጌ ማርያም ቤተክርስትያን
Pages: 1