ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 2 guests | 4 bots
Pages: 1
Posted on 01-02-18, 09:22 pm


Karma: 90
Posts: 670/838
Since: 02-29-16

Last post: 2 days
Last view: 2 days
ጋብሮቫ ፣ የታታሪዎች ፣ የቀልደኞች እና የቋጣሪዎች መኖሪያ

ቱርኮች የቦልካንን ባሕረ-ገብ መሬት ባስገበሩበት ወቅት ቡልጋሪያዊቷ፣ ወይዘሮ በዝሃና ልጆቿን ይዛ ከቬሊኮ ቱርኖቫ (የቡልጋሪያ ርዕሰ ከተማ) አንደተሰደደች አፈታሪክ ይናገራል። ከቡልጋሪያዊቷ ልጆች አንደኛው ራቾ ይባል ነበር:: ቀጥቃጩ ራቾ የሰፈረውም በድንጋያማው ያንትራ ወንዝ ዳርቻ ነበር። ራቾ የቆረቆራት መንደር ባሁኑ ጊዜ ጋብሮቮ ትባላለች:: ለቆርቋሪዋ ራቾ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ፣ የጋብሮሾን ከተማ ሰንጥቆ እሚያልፈው ያንትራ ወንዝ መኻል ባለች ደሴት ላይ ሐውልት ቆሞለታል። ቀልደኞቹ ጋብሮቮዎች ሐውልቱ ስለቆመበት ስፍራ ሲያወሱ፣ "ምንም አይነት አገልግሎት ሊሰጥ የማይችል ቦታ ነው" ይላሉ።
የጋብሮቮ ምድር ጭንጫነት የተወላጆቹን ሕይወት እጅግ ድካም የበዛበትና መራራ አድርጐት ነበር፡: ለዚህም ሳይሆን አይቀርም፣ ጋብሮቮውያን ታታሪዎች፣ የፈጠራ ሰዎችና ቀልደኞች ለመሆን የበቁት።
ጋብሮቮ፣ ባሁኑ ወቅት የተለያዩ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን በማፍራት ከሚታወቁት ግንባር ቀደም የቡልጋሪያ አውራጃዎች አንዷ ናት። ያህም ሆኖ የጋብሮቮ ተወላጆች በክረምት ወራት ድመቶቻቸው ወደ ቤት ሲገቡም ሆነ ሲወጡ በፊት ውስጥ የተጠራቀመውን ሙቀት እንዳያስወጡ "ጭራዎቻቸውን ይቆርጡዋቸዋል" ይባላል። ከዚህ አነጋገር በመነሳት ይመስላል፣ ጭራ ቆራጣ ድመት በየሁለት አመት አንዴ ለሚካሄደው አለማቀፋዊ የቀልድና ምፀት ሥነ ጥበባዊ ውድድር ፣ እንዲሁም ለቀልዶችና ምፀቶች ፌስቲቫል አርማ ሆና የምታገለግለው።
Pages: 1