ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Health - ጤና. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 01-01-18, 12:10 am


Karma: 100
Posts: 386/426
Since: 07-12-15

Last post: 37 days
Last view: 37 days
የስኳር እጥረት (Hypoglycemia)

ስኳር የሰዉነታችን ዋነኛ የኃይል ምንጭ ነዉ፡፡ በህክምናዉ በሰዉነታችን ዉስጥ የስኳር እጥረት ተከሰተ የምንለዉ በደማችን ዉስጥ ያለዉ የስኳር(ግሉኮስ) መጠን መኖር/መገኘት ከሚገባዉ መጠን በታች ሲሆን ነዉ፡፡ የስኳር እጥረት በራሱ ህመም አይደለም ነገር ግን የህመም መገለጫ ነዉ፡፡ የአንድ ጤነኛ ሰዉ ትክክለኛ የደም ዉስጥ የስካር መጠን ከ70 ሚግ እስከ 100 ሚግ ይደርሳል፡፡

የስኳር እጥረት ምልክቶች

መኪና ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመንቀሳቀስ ነዳጅ እንደሚያስፈልገዉ ሁሉ ሰዉነታችንና አዕምሮአችን በትክክል መስራት እንዲችል የማይዛባና ተከታታይነት ያለዉ የስኳር( ግሉኮስ) አቅርቦት ያስፈልገዋል፡፡ በሰዉነታችን ዉስጥ ያለዉ የስኳር መጠን በሚቀንስበት ወቅት የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ሊታዮ ይችላሉ፡፡

• የልብ ትርታ መጨመር
• ድካም
• የቆዳ መገርጣት
• የሰዉነት መራድ/መንዘፍዘፍ/መንቀጥቀጥ
• ጭንቀት
• የሰዉነት ማላብ
• የረሃብ ስሜት
• መነጫነጭ
• በአፍ ዙሪያ የሚጠዝጥዝ ስሜት መሰማትና
• በእንቅልፍ ወቅት የማልቀስ ስሜት የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

የስኳር እጥረቱ እየተባባሰ ከመጣና እርምጃ ካልተወሰደ የሚከተሉት ምልክቶች ይታያሉ

• የመዘባረቅ፣የባህሪ ለዉጥ ወይም ሁለቱም ፤መደበኛ የቀን ተቀን ስራዎን ማከናወን ያለመቻል
• እይታዎ ላይ ብዥ ማለት
• እንደሚጥል ህመም ማንቀጥቀጥ
• እራስን ሙሉ በሙሉ መሳት ናቸዉ፡፡

የችግሩ መንስኤዎች

የስኳር እጥረት የሚከሰተዉ በደምዎ ዉስጥ ያለዉ የስኳር መጠን እጅግ በጣም ሲወርድ ነዉ፡፡ ይህ እንዲከሰት የሚያደርጉ ብዙ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን በብዛት አንዲከሰት የሚያደርጉት ግን የስኳር ህሙማን የሚወስዷቸዉ የስኳር ህክምና መድሃኒቶች ናቸዉ፡፡ የስኳር እጥረት የስኳር ህመም በሌላቸዉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ቢሆንም የመከሰቱ ሂደት ግን የስኳር ህመም እንዳላቸዉ ሰዎች ግን አይበዛም፡፡

• መድሃኒቶች፡ የስኳር ህመም መድሃኒቶች፣ የወባ ወድሃኒቶች በተለይ ክዊኒን፣ በህፃናት ወይም አዋቂዎች ላይ ላይ ደግሞ የኩላሊት መስራት ማቆም(ሬናል ፌይለር ሲከሰት) በሚከሰትበት ወቅት የሚሰጡ መድሃኒቶች

• ከመጠን ያለፈ አልኮሆል/መጠጥ የሚወስዱ/የሚጠጡ፡ በተለይ በአግባቡ ሳይመገቡ መጠጣት
• ከፍ ያሉ ህመሞች መኖር/መከሰት ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡
• የሰዉነት ትኩሳት
• የምግብ ለዉጥ
• እንፌክሽን
• መፆም፡ የሆርሞን ችግሮችና የመሳሰሉት

ወዲያዉ ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች

ለመጀመሪያ ጊዜ ሊደረግ የሚችል ህክምና እንደ ህመሙ ምልክቶች ሊለያይ ይችላል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ምልክቶቹን ለማከም ከ15 እስከ 20 ግራም የሚሆን በፍጥነት ከአንጀታችን ሊመጠጡ የሚችሉ እንደ ከረሜላ፣ የፍሩት ጅስ፣ ለስላሳ የመሳሰሉትን በፍጥነት መዉሰድ/መስጠት ይመከራል፡፡ አሁኑኑ ሼር ያድርርጉት

.....................
source - hello ethiopia

Pages: 1