ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Surprising Things ገራሚ ነገሮች . | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 01-01-18, 12:04 am


Karma: 100
Posts: 385/426
Since: 07-12-15

Last post: 66 days
Last view: 66 days
የንስር አሞራ አስገራሚ ተፈጥሮ

ምርጥ ታሪክ… ይወዱታል… ሼር ያድርጉት

ንስር አሞራ ከአዕዋፋት ዘር 70 ዓመት መቆየት የሚችል የእድሜ ባለጸጋ ነዉ። ግና የእድሜው 40 ሲሆን ተፈጥሮ ሁለት አማራጮችን በፊቱ ታቀርብለታለች፤ መሞት ወይም እድሜውን ቀጥሎ ወደ 70 አመት ለመገስገስ ጠንካራ መሰናክሎችንና ስቃይ ተሞላበትን አስቸጋሪ የለውጥ ሂደቶችን ማለፍና ሌላ 30 አመትን መቀዳጀት፡፡

ንስር አሞራ ከውልደቱ/ ከተፈለፈለ/ ጀምሮ 40 ዓመት ከኖረ በኋላ ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል፡፡ አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል፡፡ ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት፤ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል፡፡

በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ ንስር አሞራ በሁለት ዉሳኔዎች አጣብቂኝ ውስጥ የሚወድቀው፡፡ ይኸውም ከዚህ ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ፤ ወይም 5 ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋእትነትን ከፍሎ ቀሪውን 30 አመቱን መውለድ፡፡

የንስር አሞራ ከቀረበለት 2 ምርጫ ቀሪ 30 ዓመቱን መቀጠል ከሆነ ምርጫው የሚከተሉት አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ያልፋል፡፡ ይኸውም ከፍተኛ ተራራ ላይ በመዉጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል። ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ መጣል ነው፡፡ ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ያወጣለታል ፡፡ መንቁሩእስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡

አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል ።አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደመሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል። ይህን 5ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡ በእድሜው ላይ 30 አመት ጨምሮ በበረራው ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ከፍ ብሎ እየበረረ ህይወትንና ደስታን በውሳኔው በቀጠለው 30 አመት ሙሉ በከፍታዎች ሁሉ ላይ በድል፣ በግርማና በሞገስ ይበራል ፡፡

ከታሪኩ ምን ተማሩ?

እንደንስር ወደላይ ወደላይ ወደላይ ……….. ምርጥ ታሪክ… ሼር ያድርጉት


ምንጭ - ኩሪ አየለ ኃይሌ

Posted on 01-01-18, 09:59 am


Karma: 100
Posts: 326/365
Since: 07-14-15

Last post: 244 days
Last view: 244 days
Des yelal Melu 1 mokeshe alege Neaser yewedla betam lesu asegobegewalew!
Posted on 01-04-18, 08:03 am


Karma: 100
Posts: 391/426
Since: 07-12-15

Last post: 66 days
Last view: 66 days
eshi abrish
Pages: 1