ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 12-31-17, 07:30 am


Karma: 100
Posts: 539/736
Since: 03-20-17

Last post: 27 days
Last view: 27 days
ሰሞኑን ምን ተከሰተ መሰላችሁ... አንድ ጓዳኛዬ ለረዥም ጊዜ የሚወዳት ልጅ አለችው…… ልጁ ምንም አይነት ገንዘብ የለውም
ነበርና እንዲሁ በሩቁ ነው የሚያፈቅራት... እሷም በጣም እንደሚወዳት ብታውቅም ቀርባው አታውቅም…… ከዛም የሆነ
ሰዓት ላይ ይሄ ጓደኛዬ የኩላሊት ህመምተኛ ሁኖ አልጋ ላይ ወደቀ... ህመሙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ በየቦታው ለሱ ማሳከሚያ በሚል ገንዘብ ማሰባሰብ ጀመርን…… ከሁለት ወር ድካምና ልፋት በኃላ ለህክምናው የሚያፈልገውን አንድ ሚሊየን
ብር መሰብሰብ ስለቻልን ወደ ውጭ ሂዶ እንዲታከም ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀመርን……
,
በዚህ ሰዓት ይሄ ታማሚ ጓደኛዬ ከሁሉም በፊት ለልጅቱ ያለውን ፅኑ ፍቅር መግለፅ እንደሚፈልግ ስላስገደደን ልጅቱ ተጠራች....
ከዛም ምን ያህል እንደሚወዳት፣ እንደሚመኛት እየነገራት እሷም በሃዘኔታ እምባዋን መቆጣጠር እስኪያቅታት ስታደምጠው ከቆየች በኃላ አሁን ስላለው ሁኔታ አጫወትናት……
,
ህይወቱን ለማዳን ለህክምናው የሚፈጀውን አንድ ሚሊየን ብር በራሱ ስም በከፈትነው አካውንት መሰብሰብ እንደቻልን ነግረን፣
ይበልጥ ተስፋ እንዲኖራትና እንድታምን ገንዘቡን የያዘውን የባንክ ቡክ ደብተር ሰጥተን በማሳየት…… «እስኪ የሚሰማሽን
ትክክለኛ ስሜት ሳትደብቂ ንገሪን…… ይሄን ያህል ጊዜ ያፈቀረሽን
ይሄን ልጅ ታገቢዋለሽ ወይስ አታገቢውም?» ብለን ጠየቅናት.....
,
እሷም በሃዘኔታ የቡክ ደብተሩን ትኩር ብላ እያየች በእምባ
የረጠቡ አይኖቿን በነጠላዋ ከጠረገች በኃላ እንዲህ
አለችን………
,
,
,
,
,
«ካልታከመበት አገባዋለሁ» ሳበሳ
Pages: 1