ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing አማርኛ. | 2 guests
Pages: 1
Posted on 12-28-17, 07:40 am (rev. 2 by ጮሌው on 12-28-17, 07:44 am)


Karma: 100
Posts: 529/751
Since: 03-20-17

Last post: 2 days
Last view: 2 days
እንቆቅልሽ/ህ ምን አውቅልሽ/ህ

አንድ ጊዜ ተዘርቶ ሁለተኛ የማይዘራ፣ ታጭዶ ምርት የማይገኝበት ምንድን ነው? ጸጉር


አንዲት ግንድ ሁለት ትክሻ ትጓደድ ምንድን ነው? ቀንበር

አንገቱ የታነቀ፣ ጅራቱ የታረቀ፣ እምብርቱን ከመሬት ያጣበቀ ምንድነው ሞፈር


ነጩ በሬ አዟሪ፣ ቀዩ በሬ በርባሪ፣ ምንድን ነው? ጥርስ፡ እና፡ ምላስ

አባ ሲሉት ቆብ የሌለው ምንድን ነው? አባ ጨንጓሬ

አፉ ዝም ብሎ በእጁ የሚናገር ምንድን ነው? ጸሐፊ

ዞሮ ዞሮ እግሩን የማይታጠብ ምንድን ነው? ከዘራ


የሰጡትን የሚበላ፣ ቢያጠጡት የሚሞት ምንድን ነው? እሳት

ስሄድ አገኘኋት ስመለስ አጣኋት ምንድን ናት? ጤዛ

ትንሽ ዕቃ ከገደል ተጣብቃ ምንድን ናት? ጆሮ

እግር እያለው ወንዝ አይሻገር ምንድን ነው? አ ል ጋ

ዞሮ ዞሮ መዝጊያው ጭራሮ ምንድን ነው? አ ይ ን

Pages: 1