ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 3 guests | 5 bots
Pages: 1
Posted on 12-27-17, 06:39 am


Karma: 100
Posts: 527/736
Since: 03-20-17

Last post: 28 days
Last view: 28 days
ዛሬ አንድ ዋይ ፋይ ያለው ሬስቶራንት አየሁኝና ለመጠቀም ገባሁ
ቁጭ
ከማለቴ አስተናጋጇ መጥታ አጠገቤ ቆመች
.
እኔ፦ የዋይፋፕ ፖስወርድ እባክሽ ንገሪኝ??
.
አስተናጋጅ፦ መጀመሪያ እዘዝ
.
እኔ፦ (ቋጣሪ እያልኩ በውስጤ) እሺ አንድ ጥብስ አልኳት
.
ከደቂቃዎች በኋላ ምግቤን በልቼ ከጨረስኩ በኋላ አስተናጋጇን
በድጋሚ ጠርቼ የዋይፋይ ፖስወርዱን ንገሪኝ እሺ??
.
አስተናጋጅ፦ መጀመሪያ እዘዝ
.
እኔ፦ (እየተበሳጨሁ) እሺ አንድ ማኪያቶ
.
ከደቂቃዎች በኋላ ማኪያቶውን ጠጥቼ ከጨረስኩ በኋላ አሁንም
ጠርቼ
እሺ አሁን ምን አባቷ ትለኝ ይሆናል እያልኩ እሺ ፖስወርዱን
ንገሪኝ??
.
አስተናጋጅ፦መጀመሪያ እዘዝ
.
እኔ፦ ከበፊቱ በጣም በመበሳጨት እንዲየውም የቤቱን ማናጀር
ጥሪው
ማናገር እፈልጋለሁ አልኳት
.
ማናጀር፦ አቤት ምን ችግር አለ አለኝ.........በትህትና
.
እኔ፦ የዋይፋይ ፖስወርዱን አስተናጋጇ አልሰጥህም ብላኝ ነው!!
.
ማናጀር፦ መጀመሪያ እዘዝ
.
እኔ፦በላሁ ጠጣሁ ከዚህ በላይ ምን እንዳደርግ ነው
የምትፈልገው
አሁን ፖስወርዱን ንገረኝ ??
.
ማናጀር፦ መጀመሪያ እዘዝ
.
እኔ፦ አረ ሰውዬ ከዚህ በላይ አንተ ብትጋብዘኝ እንኳን የመብላት
አቅም
የለኝም እባክህ ፖስወርዱን ንገረኝ
.
ማናጀር፦ አለቃዬ.....የፖስወርዱ ስም እኮ ነው "መጀመሪያ እዘዝ"
Posted on 01-05-18, 01:59 pm


Karma: 95
Posts: 707/845
Since: 07-22-15

Last post: 31 days
Last view: 8 days
ታዲያ ዝም ብለህ አታዝም
Pages: 1