ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 5 guests | 5 bots
Pages: 1
Posted on 12-26-17, 10:00 am


Karma: 100
Posts: 524/736
Since: 03-20-17

Last post: 28 days
Last view: 28 days
የሆነ ግዜ አንድ ክፍል ውስጥ የነበረ ጥያቄና መልስ ነው…
አስተማሪው ጎበዙን ተማሪና ሰነፉን አቁመው በየተራ እየጠየቁ
ነው_ሰነፉ ጎበዙን እየተከተለ ይመልሳል
መምህሩ ፦የኬንያ ፕሬዝዳንት ማን ይባላሉ?
ጎበዙ፦ጆሞ ኬንያታ
መምህሩ፦(አጨብጭቡ… ቿቿቿ)…የጋናውስ ?
ሰነፉ፦ጆምስ ጋኒያታ
( በኩርኩም!)
መምህሩ፦ ከአፍሪካ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ያላት ሃገር
ጎበዙ፦ ጋምቢያ
መምህሩ ፦(ጎበዝ)…የተረጋጋ ሰላም ያላትስ?
ሰነፉ፦ሻዕቢያ
(ተናደዱና በጥፊ)
መምህሩ ፦ አፍሪካውያንን ምን ያጋድላቸዋል?
ጎበዙ ፦ ስልጣን
መምህሩ ፦ አሜሪካውያንንስ ማን ይገላቸዋል?
ሰነፉ ፦ ቁንጣን
(በዳስተር ቆጉት)
መምህሩ፦ በኢትዮጲያ ብቻ የሚገኝ ብርቅዬ እንስሳ?
ጎበዙ፦ ዋሊያ
መምህሩ ፦ በሱዳን?
ጎበዙ ፦ ጉንዳን
(ጀርባውን በክርናቸው ደለቁት)
መምህሩ ፦የቀድሞ የግብፅ ፕሬዝዳንት ማን ይባላሉ?
ጉበዙ ፦ ሆስኒ ሙባረክ
መምህሩ፦ (አንበሳ)…የሳውዲው ንጉስስ?
ሰነፉ ፦ ኢድ ሙባረክ!
(እንሰሳ! እኔ መልስልኝ እንጂ ገጥም ግጠምልኝ አልኩህ እንዴ
ብለው ብለው በጠረባ አወረዱት )
መምህሩ፦ በሉ ይሄ የመጨረሻ ነው…በተለይ አንተ ደደብ! …
በአለም አንደኛ ሃያል አገር ማናት?
ጎበዙ፦USA
መምህሩ፦ሁለተኛዋስ?
ሰነፉ፦USB
( ይሄኔ በጣም ተበሳጭተው በቴስታ ነቀሉትና ልጁ ተዘርሮ ፌንት
ሲሰራ መምህሩ ዳይሬክተሩ ጋር ሄደው እጃቸውን ሰጡ)
Pages: 1