ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 3 guests | 5 bots
Pages: 1
Posted on 12-22-17, 07:00 am


Karma: 100
Posts: 511/736
Since: 03-20-17

Last post: 28 days
Last view: 28 days
ዙርያ ጥምጥም!
ሰውየው አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ተከሶ ፍርድቤት ቀርቧል...
ዳኛው ትእግስታቸው "አፍንጫቸው ስር "ነው የሚባሉ አይነት ሰው ናቸው ...ትእዛዝ አዘል በመሰለ ድምፅ ...<<ጊዜ ስለሌለን ጥያቄና መልሱ አጠር ባለ መልኩ ይካሄድ !! ብለው ትእዛዝ ሰጡ አቃቤ ህጉም እጅ ነስቶ ጥያቄውን ጀመረ
አቃቤ ህግ .... <<ሙሉ ስምህ ማን ነው?>>
ተከሳሽ... <<መንታ ወንድሜ ስሙ ቃየል አበራ ነው...
ዳኛው አቋረጡትና << ያንተን ስም ነው የተጠየቅከው!!?
<<መንታያው ወንድሜ ቃየል ከተባለ የኔ ስም አቤል መሆኑ የታወቀ ነው ብየ ነው ጌታዬ አቤል አበራ እባላለሁ ።
ዳኛው በአይናቸው ገርመም እያረጉት <<የወንድምህ ስም መንገሩ አስፈላጊ አልነበረም ለምትጠየቀው ጥያቄ ቀጥተኛና አጭር መልስ ብቻ ስጥ!!።
<< እሺ ጌታዬ>>
አቃቤ ህጉ ጥያቄውን ቀጠለ <<ከልጅትዋ ጋር የምትተዋወቁት የት ነው? >>
እ ...ከልጅትዋ ጋር የምንተዋወቀው.... የአክስቴ ልጅ ባል አጎት ሚስት የሚሰሩት ቦታ ላይ እርሷም አብራ ትሰራለች እና እዛ ነው የማውቃት።
<<የአክስትህ ልጅ ምናምን ምናምን ያልካቸው ሴትዮ የሚሰሩት የት ነው?
<<እሷቸው የሚሰሩት እኔ በምሰራበት መስራቤት ነው ጌታዬ>>
ዳኛው ጣልቃ ገቡና በስጨት ብለው .. እና ከልጅትዋ ጋር አብራቹ ነው የምትሰሩት ማለት ነው ?
<<አዎ ጌታዬ>>
አንተ ሰውየ ከመጀመርያው አብረን ነው የምንሰራ አትልም ወይ? .. ዙርያ ጥምጥም አትሂድ ትሰማኛለህ ? ቀጥተኛ መልስ ስጥ ተባልክኮ የምልህ ገብቶሃል?
<< አዎ ጌታዬ ገብቶኛል>> አለ ተከሳሽ እንደገባው ለማሳየት አንገቱንም ጭምር እየነቀነቀ።
አቃቤ ህጉም ካሁን ቡሗላ አጭር መልስ ካልሰጠህ ቅጣትህን ከባድ ሊያደርገው ይችላልና ቀጥተኛ መልስ ስጥ....ከልጅትዋ ጋር የነበራችሁ ግንኝነት ምን ነበር? አጭር መልስ ስጥ!!
<<አብረን ስለምንሰራ አብረን እንውላለን አብረን እንበላለን አብረን እንጠጣለን የቅርብ ጓደኛየ ነበረች አልሎትም... ከሰላምታ የዘለለ ብዙም ገነር የለንም ጌታዬ>>
ዳኛው አይናቸውን እያጉረጠረጡ በማይሰማ ድምፅ ማጉረምረም ጀመሩ....
መርማሪው በረጅሙ ከተነፈሰ ቡሗላ ጥያቄውን ቀጠለ...
ነገረሩ የተፈፀመው መቼ ነው?ለምንስ ቤትዋ ሄድክ?
ሰኞ ለስራ ከመገባቴ በፊት ሲል አቃቤ ህጉ አቋረጠውና ሰኞ ስራ ከመግባትህ በፊት ቤትዋ ሄድክ?
አይ አይደለም ሰኞ ስራ ከመግባቴ በፊት ኡሁድን ቤት መዋል እወዳለሁ እና ቅዳሜ ቀን .. ቅዳሜ ቀንም ቤት ነው የምውለው አርብ ከሰአትም እንዲሁ አረፍ እላለሁ አርብ ከሰአት ነው ጠበል ጠዲቅ ቅመስ ብላ የጠራችኝ!
ጃኛው ...አንተ ከብት የምለው አይገባህም ሰኞ እሁድና ቅዳሜ ምን አመጣቸው አርብ ከሰአት ቤትዋ ሄድኩ አትልም ወይ? ሰኞ እሁድ እያልክ ምናባክ ያጠማዝዝሃል ለጥያቄው አጭር መልስ ስጥ ማለት አማርኛ አይደለም እንዴ ??
<<አማርኛ ነው ጌታየ >>አለ ተከሻሹ አንገቱን እንዳቀረቀረ አቃቤ ህጉም ጥያቄውን ቀጠለ<< ፀበል ለመቅመስ ቤትዋ ከሄድክ ቡሃላ ምን ተፈጠረ.. ባክህ ባጭሩ መልስ ስጥ፣ አስገድደህ ደፍረሃታል ወይስ አልደፈርክም ባጭሩ መልስ?
<<ጌታየ ቤትዋ ገባሁ በላሁ ጠጣሁ እንደገና ጠጣሁ ከኛ ውጪ ሰው አልነበረም ጠላውንም ጠጅንም ቀዳችልኝ እኔም ጠጣሁ... እንዴት እንደሆና አላውቅም ጠላ ልትቀዳልኝ ስትጠጋ ጡትዋን ፍጥጥ ብሎ አየሁት !! ጌታዮ እንዴት ነዘረኝ መሰልዎት ... ከዛማ ስጋዊው ስሜቴ ተቀሰቀሰ ህፍረተ ስጋየን እንዳታየው ከለል አረኩት ሩካቤ ስጋ ለመፈፀም ገላየ ተነሳሳ ግብረስጋ ግንኝነት ካላደረክ ብሎ አንዳች ነገር ይረብሸኝ ጀመር የፍትወተ ስጋ .. እያለ ሲያወራ ዳኛው ትእግታቸውን አጡ ከተቀመጡበት ተሰፈንጥረው እየተነሱ አንተ ደንቆሮ የምን ፍርፍር የምን ስጋ እያሉ መዘላበድ ነው ከበዳህ በዳሁ አትልም
Posted on 12-22-17, 08:00 pm


Karma: 90
Posts: 660/838
Since: 02-29-16

Last post: 2 days
Last view: 2 days
hahahaha
Posted on 12-22-17, 10:45 pm


Karma: 100
Posts: 545/599
Since: 08-27-16

Last post: 1 day
Last view: 20 hours
ከአልጋ፡ወደቅሁ፡ማለት፡ይሻላል።
Posted on 12-23-17, 09:20 am


Karma: 100
Posts: 405/437
Since: 07-20-15

Last post: 21 days
Last view: 21 days
ወይ ጉድ
Posted on 12-25-17, 12:07 am


Karma: 95
Posts: 703/845
Since: 07-22-15

Last post: 31 days
Last view: 8 days
Aygermshm tg
Posted on 12-25-17, 05:04 am


Karma: 100
Posts: 408/437
Since: 07-20-15

Last post: 21 days
Last view: 21 days
germegn enji lol
Posted on 12-25-17, 11:31 am


Karma: 100
Posts: 324/365
Since: 07-14-15

Last post: 30 days
Last view: 30 days
Lol
Pages: 1