ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing አማርኛ. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 12-15-17, 06:37 am (rev. 1 by Ye Arada Lij on 12-15-17, 06:38 am)


Karma: 90
Posts: 655/879
Since: 02-29-16

Last post: 37 days
Last view: 37 days
እንቆቅልህ በግዕዝ "አንቆቅሆ" ማለት ነው። ወደ አማርኛ ሲመለስ አንቆቅሆ እንቁላል ማለት ይሆናል፤ ስለዚህ እንቆቅልህ ማለት በስረ መሰረቱ እንደ እንቁላል ድፍን የሆነ ፍቼው ያልታወቀ መመርመርን የሚጠይቅ ፈተና ማለት ነው።

እንቆቅልህ የአዕምሮ ንቃትን ይጠይቃል፤ ተጠያቄው ወይም ተፈታኙ ሰው በተወሰነ ሰዓት የምሳሌውን ፍቺ ማግኘት አለበት፤ አለዚያ አገር መስጠት እና መሰደብ ይኖርበታል። ነገር ግን በተወሰነ ደቂቃ ውስጥ ትክለኛ የሆነውን ፍቺ ያገኘ እንደሆነ አገር ከመሥጠት እና ከመሰደብ ይድናል። የአዕምሮ ዝቅተኛነትም አይሰማውም።

እንቆቅልሽ ስዕላዊ ምርመራን ይፈልጋል። ተያቂው የረቀቀ እና የበሰለ ምስጢር ያዘለ ምሳሌን ሲያቀርብ ተጠያቂው ከምሳሌው ጋራ የሚነፃፀሩትን ነገሮች ሁሉ እያሰበ ትክክለኛ ከሆነ መልስ እስኪደርስ ማውጣት፣ ማውረድ እና መመርመር የሚያሻው ነው።

ትርጉም የሚሆኑትን ነገሮች ሁሉ በአይነ አእምሮ እየተመለከተ ከምሳሌው ጎን ለጎን እየኮለኮለ ማስተያየትና ማነፃፀር ይኖርበታል። ተፈታኙ እንደ ኢላማ አነጣጥሮ ከእውነተኛው ትርጉም ሲደርስ የእንቆቅልሹ ትርጉም ይህ ነው ብሎ ይመልሳል።

በትግል አቅምን በመገመት ጉልበትን መፈተን እንደሚቻል ሁሉ በእንቆቅልሽም የአምሮን ንቃትና የአሳቡን ሃይል ማወቅ ይቻላል። ሰው ሁሉ አንድ አይነት አስተያየት የለውም፤ አንዱ ከሌላው በችሎታ ይበልጣል፤ አንዱ ደግሞ የተለየ ሥጦታ ኖሮት በአንደኛው ነገር ንቁ ሲሆን በሌላው ይደክማል። ስለዚህ አንዳንድ ልጆች ብቻ እንቆቅልሽን ቶሎ ለማግኘትና ትክክለኛ ፍቺ ለመስጠት ይችላሉ።

እንቆቅልሽ ጊዜን የሚጠይቅ የምርመራ ፈትና ነው። ይሁን እንጂ ጥያቄው በተወሰነ ደቂቃ ውስት መመለስ አለበት፤ የእንቆቅልሹ አቅራቢ "መሸብህ እንቆቅልሼ ተነዛብኽ፣ ዋለብህ አደረብህ አገር ሥጠኝ" እያለ ተጠያቂውን ይወተውተዋል፣ ያዋክበዋል።

ተጠያቂው እንቆቅልሹን መፍታት፣ ከትርጉሙ መድረስ ያቃተው እንደሆነ አገር ይሰጠዋል፤ በዚህም ድል መሆኑን እና መሸነፉን ስለሚገልፅ የአምሮ ዝቅተኛነት ይሰማልዋል፤ የእንቆቅልሹ ባለቤት በበኩሉ ይደሰታል። የአገሩን ስም እየጠየቀ አነሰኝ፣ ጨምርልኝ እያለ ያስገድደዋል፤ የሚመኘውን እና የሚፈልገውን ካገኘ በኋላ፣ እዚህ ተቀምጬ ምን አጥቼ፤ ሁሉ በእጄ፣ ሁሉ በደጄ እንዳልሰድብህ ወንድሜ እንዳተውህ ጠላቴ እያለ ይወቅሰዋል።

በዚህ ጊዜ በጠያቂውና በተጠያቂው ፊት ላይ የበላይነትና የበታችነት ስሜት ማንበብ አዳጋች አይሆንም። የእንቆቅልሹ ባለቤት በጌታ ሁናቴ፤ በሰንጋ በቅሎ ሆኜ አንተን አሽከሬን በገጣባ አህያ አስቀምጬ፣ እያለ የተሸናፊውን ዝቅተኛነት ያስረዳዋል።

ከዚህም አነጋገር ታላቅ ሚሥጥር እናገኛለን፤ ይኸውም በአዕምሮ ያልጎለመሰ የማሰብ ሃይሉ ከተፈጥሮ ጓደኛው ያነሰ ሁሉ፣ ለወንድሙ አሽከር ሆኖ መኖሩን የሚያስገነዝብ ነው።
ምንም እንኳን በቀድሞ ጊዜ ለጉልበት ስራ ብቻ ከፍተኛ ግምት ቢሰጠው፤ የአባቶቻችን የማስተዋል ንቃት፤ የመንፈስ ብርታትና የናላ ሃይል አስፈላጊ መሆኑን አልዘነጉትም። ለምሳሌ፤ጥያቄ : እንቆቅልህ? ምን አውቅልህ?
ላዩ ሰርዶ ውስጡ ብርንዶ።
መልስ: ቀይ ሽንኩርት።

ጥያቄ : እንቆቅልህ? ምን አውቅልህ?
ሲወለድ ይጠቁር፣ ሲያርጅ ይቀላ።
መልስ: በርበሬ።

ጥያቄ : እንቆቅልህ? ምን አውቅልህ?
ወተቱ ጥቁር ማለቢያው ነጭ።
መልስ: ቡና።

ጥያቄ: እንቆቅልህ? ምን አውቅልህ?
እልም ካለ ዱር ከብቼ የምቆርጠው አጥቼ።
መልስ: ጉም።

ጥያቄ: እንቆቅልህ? ምን አውቅልህ?
ልብስም ጉርስም ትሆን።
መልስ: በግ።

ምንጭ:
የብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል ስብስብ ስራዎች።
Pages: 1