ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing አማርኛ. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 12-13-17, 07:00 am


Karma: 90
Posts: 647/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
ለዳኛ አመልክት፤ እንዲሆን መሰረት።
ለወሬ የለው ፍሬ፤ ላበባ የለው ገለባ።
ማን ይመስክር የነበረ፤ ማን ያርዳ የቀበረ።
ምስክር ለበለጠ፤ ውድማ ለመለጠ።
ምስክር ከተጠራ፤ መስዋዕት ከተሰራ።
ምንዝር ሲለቅ ላለቃ፤ አለቃ ሲለቅ ለሻለቃ።
ሰማንያ ለማገጃ፤ ስለት ለማረጃ።
ሳይገሉ ጎፈሬ፤ ሣያስረግጡ ወሬ።
ስለት ድግሱን፤ ደባ ራሱን።
በሰማንያ ያለቀ፤ በፀሃይ የደረቀ።
በቆረጡት በትር ቢመቱ፤ ባወጡት ዳኛ ቢረቱ፤ የእግዜር ግቡ ከብቱ።
በተለሙ ያርሷል፤ በዠመሩ ይጨርሧል።
ባጉራህ ጠናኝ የተረታ፤ ማህል አገዳውን የተመታ።
ባፈሳ ይታፈሳል፤ በነጠረ ይመለሳል።
ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ።
ንጉስ አይከሰስ፤ ሰማይ አይታረስ።
ንጉስ የፈረደው፤ ሰይፍ የቆረጠው።
ተቀምጦ የሰቀሉትን፣ ቆሞ ማውረድ ይከብዳል።
ተዋጊ በሬህን፣ ተናካሽ ውሻህን ያዝ።
አባት ያቆየው፣ ለልጅ ይበጀው።
አንድ አይነድ፤ አንድ አይፈርድ።
ርስት በሺህ አመቱ ለባለቤቱ።
እውነት የተናገረ፤ በመርከብ የተሻገረ።
ከራስ ወዲያ መስካሪ፤ ከእግዜር ወዲያ ፈጣሪ።
ከኑግ የተገኘን ሰሊጥ፤ አብረህ ውቀጥ።
ካነጋገር ይፈረዳል፤ ካያያዝ ይቀደዳል።
አሳ ጎርጏሪ ዘንዶ ያወጣል፤ የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል።
የሞተ አይከሰስ፤ የፈሰሰ አይታፈስ።
የሥራት መቇሚያው ፈጠም፤ የስጋ መቇሚያው ቅልጥም።
የተበደለ ከነጋሽ፤ የተጠማ ከፈሳሽ።
የንጉስ ቃል የቆመ ይጥላል፤ የተቀመጠ ይፈነግላል።
ያባት እዳ ለልጅ፤ ያፍንጫ እድፍ ለእጅ።
ያዋቂ ኣጥፊ፤ የእስራዔል ጣፊ።
ከድሎ ካለቃዬ፤ ከሶ ከጠበቃዬ።
ግፍ የተሰራ በኛ፤ ካሱ ይሉናል በዳኛ።

ምንጭ:
የብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወ/መስቀል ስብስብ ስራዎች
Pages: 1