ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Trains . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 12-11-17, 06:24 am


Karma: 90
Posts: 644/887
Since: 02-29-16

Last post: 176 days
Last view: 176 days
አስሩ የዓለማችን ፈጣን የምድር ባቡሮች
በአሁኑ ጊዜ የባቡር ትራንስፖርት በመላው ዓለም ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ዋንኛ አማራጭ ሆኗል። በዚህም ሳቢያ እጅግ ፈጣን የሆኑ ባቡሮች ወደ ገበያ እየገቡ ይገኛሉ። ሬልዌይ ቴክኖሎጂ ድረ-ገፅም የአለማችን ፈጣኖቹ እና በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ ያሉ ያላቸውን አስር ፈጣን የምድር ባቡሮች ያስቀምጣል።
1. ሻንጋይ ማግሌቭ - ይህ የምድር ባቡር ወደ ስራ የገባው እ.ኤ.አ. በ2004 ነበር። ባቡሩ በሰዓት 430 ኪሎ ሜትሮችን በመክነፍ በቀዳሚነት ተቀምጧል። ባቡሩ ከሎንግያንግ ጣቢያ እስከ ሻንጋይ ፑዶንግ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያም መንገደኞችን አሳፍሮ በዚህ ፍጥነት ይፈተለካል።
2. ሀርመኒ ሲአርኤች 380ኤ - ይህ የምድር ባቡር በሁለተኛ ደረጃ ሊቀመጥ የቻለው ፍጥነቱ በሰዓት 380 ኪሎ ሜትር በመሆኑ ነው። እ.ኤ.አ. በ2010 ስራ የጀመረው ይህ የምድር ባቡር ከቤጂንግ እስከ ሻንጋይ ድረስ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፤ ከውሃን እስከ ጉያንግዡ ባሉት መስመሮች በየእለቱ አገልግሎት ይሰጣል።
3. ኤጂቬ ኢታሎ - ይህ የምድር ባቡር ወደ ስራ የገባው በ2012 እ.ኤ.አ. ሲሆን፤ ያለው ፍጥነትም በሰዓት 360 ኪሎ ሜትሮች ነው። ይህ በአውሮፓ እጅግ ዘመናዊ የተባለው የምድር ባቡር በናፖሊ፣ ሮማ፣ ፍሬንዜ እና ቦሎኛ አድርጎ እስከ ሚላኖ ይጓዛል።
4. የሲሜንስ ቬላሮ ኢ - ይህ ኤቪኢ 103 በሚል የተሰየመው የምድር ባቡር የስፔን ባቡር ሲሆን፤ ፍጥነቱም በሰዓት 350 ኪሎ ሜትር ነው። ባቡሩ ተሰርቶ የተጠናቀቀው በ2005 ሲሆን፤ ወደስራ የገባውም በ2007 ነው።
5. ታልጎ 350/ቲ 350 - ይህ የምድር ባቡር ያለው ፍጥነት በሰዓት 350 ኪሎ ሜትሮችን ነው። ወደ ስራ የገባውም እ.ኤ.አ. በ2005 ነበር። የምድር ባቡሩም አገልግሎት የሚሰጠው ከማድሪድ ዛራጎዛ እስከ ሊዳ ባሉት የስፔን ከተሞች ነው።
6. ኢያ ሲሪስ ሺንካንስን ሃያቡሳ - ይህ የጃፓን የምድር ባቡር ወደ ስራ የገባው እ.ኤ.አ. በ2011 ሲሆን በሰዓት 320 ኪሎ ሜትሮችን መምዘግዘግ ይችላል።
7. አልስቶም ኢሮዱፕሌክስ - ይህ በ2011 ወደ ስራ የገባው የምድር ባቡር በሰዓት 320 ኪሎ ሜትሮች በአውሮፓ ምድር ይመዘገዘጋል። ይህ 1ሺህ20 ሰዎች የሚያጓጉዝ ባቡር ባለቤትነቱ የፈረንሳይ ነው።
8. ቲጂቪ ዱፕሌንክስ - ይሄን ባቡር ለመስራት ከ1996 እስከ 2008 (እ.ኤ.አ) ጊዜ ወስዷል። ባቡሩ በሰዓት ከ300 እስከ 320 ኪሎ ሜትሮችን ይጓዛል። ክብደት እንዳይኖረው ታስቦ ከአሉሚኒየም የተሰራው ይህ ባቡር በአንድ ጊዜ 512 መንገዶችን የሚያጓጉዝ የፈረንሳይ ባቡር ነው።
9. ኢቲአር 500 ፍሬክይሮሳ - ይህ በ2008 ወደ ስራ የገባ የምድር ባቡር ፍጥነት በሰዓት 300 ኪሎ ሜትር ነው። አገልግሎት የሚሰጠውም በሮምና በሚላን ከተሞች መካከል ባሉት መስመሮች ነው።
10. ቲኤችኤስ አር 700ቲ - ይህ በታይዋን ታይፒ እና ከውሲውንግ መካከል አገልግሎት የሚሰጥ ባቡር ፍጥነቱ በሰዓት 300 ኪሎ ሜትር ሲሆን፣ ወደ አገልግሎት የገባውም እ.ኤ.አ. በ2007 ነው።

Posted on 12-11-17, 10:37 am


Karma: 95
Posts: 689/852
Since: 07-22-15

Last post: 59 days
Last view: 10 days
Yegnaw sntegnaw new
Posted on 12-14-17, 07:56 am


Karma: 100
Posts: 401/444
Since: 07-20-15

Last post: 313 days
Last view: 313 days
ante fikir ahun ezi akababi yegna sim yiteral lol
Posted on 12-14-17, 08:38 am


Karma: 95
Posts: 695/852
Since: 07-22-15

Last post: 59 days
Last view: 10 days
Mn chgr alew ezih akababi egna bcha aydel endea yalenew tgeay endewm enea ena anchi bcha new yalenew mn ylenal
Posted on 12-15-17, 04:37 am


Karma: 100
Posts: 404/444
Since: 07-20-15

Last post: 313 days
Last view: 313 days
minim
Posted on 12-15-17, 07:50 am


Karma: 95
Posts: 697/852
Since: 07-22-15

Last post: 59 days
Last view: 10 days
Eko tgyea
Pages: 1