ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Ethiopian News & Events አዲስ ዜና. | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 12-09-17, 08:39 pm (rev. 1 by Ye Arada Lij on 12-09-17, 08:44 pm)


Karma: 90
Posts: 642/879
Since: 02-29-16

Last post: 69 days
Last view: 69 days
-በሰይፉ-ፋንታሁን-ላይ-የክስ-አቤቱታ-አቀረበ
“የድርጅቱ ስም ጠፍቷል፤ ህልውናዬም አደጋ ላይ ወድቋል”
“በሬዲዮ ፕሮግራም የድርጅቱ ስም ጠፍቷል፤ ህልውናዬም አደጋ ላይ ወድቋል” ያለው ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ ቤት፤ በታዋቂው የሬዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን ላይ የክስ አቤቱታ አቀረበ፡፡
የባህል ምግብ ቤቱ ባለቤት፣ የባህል አምባሳደሩ አቶ ትዕዛዙ ኮሬ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባስገቡት የአቤቱታ ማመልከቻ ላይ፤ በኤፍኤም 102.1 ሬዲዮ ስርጭት ላይ በአቶ ሰይፉ ፋንታሁን ፕሮግራም ከስቱዲዮ በቀጥታ ወደ ባህል ምግብ ቤቱ ስልክ በመደወል፣ ለ20 የቻይና እንግዶች በ10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የውሻ ስጋ ጥብስ እንዲዘጋጅለት የፕሮግራሙ አዘጋጅ ጥያቄ ማቅረቡ ተጠቅሷል፡፡
ድርጅቱም ለፕሮግራሙ አዘጋጅ የሰጠውን መልስ ሲገልጽ፤ ”ድርጅቱ ይህን የመሰለ ለሀገሪቱ ባህልና እምነት አፀያፊ የሆነ ተግባር እንደማይፈፅምና ወደፊትም እንደማይደረግ የማያዳግም ምላሽ ተሰጥቶታል” ይላል። ይሁን እንጂ ፕሮግራሙ በቀጥታ በአየር ላይ በመዋሉ ደንበኞች በድርጅቱ የምግብ አቅርቦት ላይ ብርቱ ጥርጣሬ እንዲፈጠርባቸው አድርጓል ብሏል - በአቤቱታ ማመልከቻው፡፡በጉዳዩ ላይ አዲስ አድማስ ማብራርያ የጠየቀው የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን፤ ፕሮግራሙ ፕራንክ ፎን በተሰኘው የሬዲዮ ፕሮግራም ከ8 ዓመት በፊት የተላለፈ መሆኑን ጠቁሞ፣ “በወቅቱም ምግብ ቤቱ የተጠየቀው ተግባር እንደማይደረግ መገለፁን ተከትሎ፣ የድርጅቱን መልካም ስምና ተግባር የሚያጎላ ፕሮግራም ነው የተላለፈው እንጂ ፈፅሞ ጉዳት የሚያደርስ አይደለም፤ ይህንንም የትኛውም አካል ፕሮግራሙን በድጋሚ በኢንተርኔት አማካኝነት አዳምጦ መረዳት ይችላል” ብሏል፡፡
“ፕሮግራሙ በቅንነት የተሰራ ነው፤የተላለፈው መልዕክት ስለ ዮድ አቢሲኒያ ትልቅነት የሚያወሳ እንጂ በተባለው መንገድ ጉዳት የሚያደርስ አይደለም” ሲልም አስተባብሏል - ሰይፉ፡፡
የዮድ አቢሲኒያ አቤቱታ ግን በዚህ ብቻ አያበቃም። ከሬዲዮ ፕሮግራሙ ውጭ በቅርቡ ህዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ በማህበራዊ ድረ ገፅ፤ “ቻይናዊው ዮድ አቢሲኒያ ውሻ ሊያስጠብስ ታዲያስ አዲስ ሸወደ” በማለት ከ5 ቻይናውያንና ከአቶ ሰይፉ ፋንታሁን ጋር የሚታይ ፎቶ ለህዝብ በማሰራጨት ድርጅቱ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያገኘውን ታዋቂነት እጅግ የሚያረክስ ዘመቻ ተከፍቶበታል ይላል።
“በዚህ መልኩ በድርጅታችን ህልውና ላይ የተሰነዘረው ጥቃት፣ ከኢንፎርሜሽንና መረጃ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) በሚቀርብ የሙያ አስተያየትና ድርጅቱ በሚያቀርባቸው ማስረጃዎች፣ ምርመራ ተጣርቶ ለህግ ይቅረብልኝ” ሲል ድርጅቱ አቤቱታውን ህዳር 26 ቀን 2010 ዓ.ም ለፖሊስ በፃፈው ደብዳቤ አቅርቧል፡፡
የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን በበኩሉ፤ “እኛ በፌስ ቡክ ያሰራጨነው ምንም መረጃ የለም፣ ሌሎች አድርገውት ሊሆን ይችላል፤ ይሄ ከኛ ቁጥጥር ውጪ ነው” በማለት ስለ ጉዳዩ እንደማያውቅ አስረድቷል፡፡ አክሎም እንደገለጸው፤ “በጉዳዩ ላይም ከዮድ አቢሲኒያ ሊያነጋግረን የሞከረ አካል የለም፤ ችግሩን በመነጋገር ለመፍታት ዝግጁ ነን” ብሏል - ሰይፉ ፋንታሁን፡፡

ከአዲስ አድማስ ዜና
Posted on 12-10-17, 08:47 pm


Karma: 95
Posts: 683/850
Since: 07-22-15

Last post: 89 days
Last view: 1 day
Ay seyfsha ende ebd wsha hulum lay ydersal aydel?
Pages: 1