ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Transportation - መጓጓዣ. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 12-09-17, 08:23 am


Karma: 90
Posts: 641/887
Since: 02-29-16

Last post: 373 days
Last view: 373 days
ባዮ ፊዩል ቤንዚንም ናፍጣም ነው !

ባዮ ፊዩል በሁለት ይከፈላል - ባዮ ኢታኖልና ባዮ ዲዝል ። ’’ባዮ ኢታኖል ’’ በፈሳሽ መልክ ከሚመረቱ የባዮ ፊዩል ዓይነቶች አንዱ ነው ። ኢታኖል በስኳር ፋብሪካዎች የሚመረት ሲሆን በማብላላት (Fermentation) አማካኝነት ወደ አልኮል በመለወጥና በማጣራት (Distillation) የሚገኝ ፈሳሽ ነዳጅ አልኮል ነው ።
የኢታኖል ምርት በሁለት ይከፍሉታል ። አንደኛው ቴክኒካል አልኮል ሲሆን ሁለተኛው ፖወር አልኮል ይባላል ።
ፖወር አልኮል ከቤንዚን ጋር ተቀይጦ ለተሽከርካሪዎች አገልግሎት ይውላል ። ቴክኒካል አልኮል ደግሞ ለአረቄ ፋብሪካዎችና ሌሎች የኢንዱስትሪ ዘርፎች በግብአትነት ያገለግላል ።
ሁለተኛው የባዮ ፊዩል ዘርፍ ’’ ባዮ ዲዝል ’’ ነው ። ባዮ ዲዝል ከተለያዩ የእፅዋት ዘይቶች የሚዘጋጅና ሙሉ በሙሉ ወይም ከናፍታ ጋር ተቀይጦ ለትራንስፖርትና የተለያዩ የናፍታ ሞተሮችን ማንቀሳቀስ ይችላል ።
ይህ ታዳሽ የሃይል ምንጭ ለትራንስፖርት ፣ ለውሃ መሳቢያ ፣ ለኩራዝ መብራት ፣ ለወፍጮና በገጠር አካባቢዎች ለኤሌክትሪክ ጀነሬተር ማንቀሳቀሻ ያገለግላል ያሉት በማእድን ፣ የነዳጅና የተፈጥሮ
’’ ባዮ ዲዝል ’’ ጃትሮፋ ፣ ጉሎ ፣ አኩሪ አተር ፣ ፖንጋሚያ ፣ ኦይል ፖምና ብሳና ከመሳሰሉ ዛፎችና ሰብሎች የሚመረት ነው ። ጃትሮፋ ፣ ጉሎና ብሳና ደግሞ ለዘርፉ ልማት እጅግ ተመራጮች ናቸው ። በተለይ ጃትሮፋ ለባዮ ዲዝል ልማት ቁንጮ ነው ይሉታል ።
ጃትሮፋ ሳይንሳዊ ስሙ ጃትሮፋ ኩርካስ ይባላል ። በአገራችን አንዳንድ አካባቢዎች ’’ አይደርቄ” ይሉታል ። ’’ ሽማግሌው አጥር ” እያሉ የሚጠሩትም አሉ ። ጃትሮፋ ከቅንጭብ ፣ ቁልቋል ፣ ጉሎና የጎማ ዛፍ ቤተሰብ ውስጥ ይመደባል ።
ጃትሮፋ መሰረቱ መካከለኛው አሜሪካ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ ።በፖርቹጋላዊያን አሳሾችና ቅኝ ገ¡ዎች በኬብ ቨርዴ በኩል ወደ አፍሪካና ኤሲያ እንደተሰራጨም ይነገራል ። በአሁኑ ጊዜ የምድር ወገብን ተከትሎ በበርካታ አገራት ተሰራጭቶ ይገኛል ።
ጃትሮፋ ፣ ጉሎና ብሳና የመሳሰሉ ተክሎች በአገራችን ናፍታን ለመተካትና ለመቀየጥ ከሚሰጡት አገልግሎት የዘለለ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉዋቸው ። የሚተከሉት ለምግብ ሰብል ልማት አገልግሎት በሚሰጥ የእርሻ ማሳ ሳይሆን በምድረ በዳና ተራራማ አካባቢዎች ነው ።
ለባዮ ዲዝል ግብአትነት ከሚሰጡት ምርት ባሻገር አካባቢን መልሶ የማልማትና የደን ሽፋናችንን በማሳደግ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ ይጠቅማሉ ባይ ናቸው ። ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ያላቸው ፋይዳም የጎላ ነው ።
የባዮ ዲዝል ዘርፍ ሰፊ የስራ እድል ይፈጥራል ። ከተረፈ ምርቱ መካከል ጀንፈሉን በከሰል መልክ በማዘጋጀት ለማብሰያ አገልግሎት በማዋል የደን ምንጣሮን ይከላከላል ። ገለባውና ጭማቂው ለአፈር ለምነት ይጠቅማል ።
Posted on 12-10-17, 08:55 pm


Karma: 95
Posts: 687/852
Since: 07-22-15

Last post: 256 days
Last view: 172 days
Wey bio arif new
Pages: 1