ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Men's Health . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 12-02-17, 07:36 am


Karma: 90
Posts: 638/879
Since: 02-29-16

Last post: 34 days
Last view: 34 days
✔እንደው ሳታነቡት እንዳታልፉ
✔ካነበባችሁ በኋላም ሼር አርጉ
✔የተሰማችሁንም ስሜታችሁን በኮሜንት ጻፉልኝ
ወረድ ብላችሁ ማንበብ ጀምሩ!
"የ105 አመት አዛውንት ናቸው መሽናት እስኪያቅታቸው ድረስ ኩላሊታቸውን ያማቸውና ሆስፒታል ይሄዳሉ፡፡ ዶክተሩ ከህመማቸው እንዲድኑ ቀዶ ጥገና መደረግ እንዳለባቸው ይወስናል፤ አዛውንቱም ተስማምተው ቀዶ ጥገና ተደረገላቸው፡፡
ቀዶ ጥገናው ተጠናቆ አዛውንቱ ህመማቸው መለስ ብሎላቸው ከሆስፒታል ሲወጡ እስካሁን ለህክምናቸው የወጣውን ወጪ የሚያሳይ ቢል ዶክተሩ አምጥቶ ይሰጣቸዋል፡፡ ;
አዛውንቱ ቢሉን ሲያዩ ድንገት እንባቸው ፍንቅል ብሎ በፈዘዙ አይኖቻቸው መፍሠሥ ጀመረ እጅግ በጣም የመረረ ለቅሶ አለቀሱ፤ ዶክተሩ ማልቀሳቸውን ሲያይ ሊያጽናናቸው ሞከረ
“ገንዘቡ ከብድዎት ነው አይዞት ከሠዎች ሠባስበን አንድ ነገር እናደርግልዎታለን አያልቅሱ” አላቸው፡፡
ሰውየው ቀና ብለው ዶክተሩን እያዩ
“እኔን ያስለቀሰኝ የገንዘቡ ብዛት አይደለም! ፈጣሪ 105 አመት ሲያሸናኝ አንድም ቀን የክፍያ ቢል አልላከብኝ!
እሱ ነው ያስለቀሰኝ ልጄ”አሉት፡፡:
ሲገርም!
ፈጣሪ ለኛ የሰጠን ስጦታ እንዲህ በቀላሉ ተቆጥሮ የሚያልቅ አይደለም::
የማይከፈልበት :- አይን
የማይከፈልበት :-እጅ
የማይከፈልበት :-እግር
በዛ ላይ የሰው ልጅ አድርጎ እንዲህ አሳምሮ ፈጠረን!!!:
አብዛኞቻችን ፈጣሪያችንን የምናመሰግነው ጥሩ ነገር ስናገኝ ብቻ ነው፡፡ እስኪ ሁሌም ፈጣሪያችንን ስለሰጠን ስላልሰጠንና ስለሚሰጠን፣ስለሰራልን ስላልሰራልንና ስለሚሰራልን፣ ስላደረገልን ስላልተደረገልንና ስለሚደረግልን ነገር ሁሉ እናመስግነው!!!
(ካነበብኩት)
Posted on 12-02-17, 02:29 pm


Karma: 100
Posts: 487/610
Since: 08-27-16

Last post: 49 days
Last view: 7 days
የሁሉ፡ቀን፡ምስጋናዬ፡ባጭሩ፡
ክብሩ፡ይስፋ፡ለመድሃኒዓለም፡
የባሰ፡አታምጣ፡የበታችህን፡እንጂ፡የበላይህን፡አትይ፡ነው።
Pages: 1