ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Ethiopian News & Events አዲስ ዜና. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 11-29-17, 08:31 am


Karma: 100
Posts: 485/760
Since: 03-20-17

Last post: 18 days
Last view: 3 days
ከሰሞኑ በማህበራዊ ድረገጾች ላይ መነጋገሪያ
የሆነው ድምጻዊ ተመስገን ገብረ እግዚአብሔር ነው። አንዲት በስዊዘርላንድ የምትኖር ወጣት የመልበሻ ክፍሉ ድረስ አድናቂ መስላ በመግባት አስገድዳ እንደመሳም አድርጋ የተነሳችውን ፎቶ በመልቀቅ የድምጻዊውን መልካም ገጽታ ለማጥፋት
መሞከሯ መነጋገሪያ ሆኗል። እነዚህ ፎቶዎች መለቀቃቸውን
ተከትሎ በአውሮፓ እየተዘዋወረ ሥራዎቹን በማቅረብ ላይ የሚገኘው ድምጻዊው በፌስቡክ ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት እንዲህ ብሏል:-

የተከበራቹ አድናቂዎቼ በሙሉ
ከታች የምትመለከቱት ፎቶ በ June 27,2014 በ ዙሪክ
(Zurich, Swiss) በነበረኝ ኮንሰርት ላይ የመድረክ ስራዬን ጨርሼ ባክ ስቴጅ ከመግባቴ ገና ከላዬ ላይ ያለው ላብ ሳይደርቅ አድናቂዎቼ ከኔ ጋር ፎቶ ለመነሳት ከገቡት ውስጥ ይቺ ፎቶ ላይ የምትመለከቷት ወጣት ከኔ ጋር ፎቶ እንድትነሳ በጠየቀችኝ መሰረት አብረን ፎቶ ለመነሳት ባረገችው ከልክ ያለፈ አድናቆቷን ባከብርላትም ፣ ነገር ግን ከልክ ያለፈ የፎቶ አነሳሷን አልተቀበልኩትም ነበር።
በነበረው ግርግር እንዲህ ማድረግ እንደሌለባት እየነግርኳት ባለው ሰዓት ውስጥ ፎቶው ተነስቶ ነበር።
እኔ አድናቂዎቼን የማከብር ከመሆኑም ባሻገር አግባብ ባለው ሁኔታ ከአድናቂዎቼ ጋር ፎቶ መነሳትን አከብረዋለው። ሆኖም ግን በተገቢውና ባግባቡ ሲሆን ብቻ ነው። ስለዚህ ይህ ፎቶ ከኔ ፍላጎት ውጪ የተደረገ በመሆኑ አልተቀበልኩትም ፣
አድናቂዎቼም በእኔ ላይ መጥፎ አመለካከት እንዲኖራቸውም አልሻም።
ተመስገን ገ/እግዚአብሔር (ተሙ)

Pages: 1