ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing ልጅነት. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 11-22-17, 07:41 am (rev. 1 by ጮሌው on 11-22-17, 07:44 am)


Karma: 100
Posts: 474/769
Since: 03-20-17

Last post: 409 days
Last view: 409 days
ልጅ_እያለሁ ፦
ልጅ እያለው ሰርግ ላይ “ብር አንባር ሰበረልሽ… " ተብሎ
ሲዘፈን
የሙሽራዋን የእጅ አንባር ባልየው የሰበረው ይመስለኝ ነበር
.
.
.
.
እማዬ "ሰላም ያዋልከን ሰላም አሳድረን! ?…" ብላ
ወደመኝታችን
ልንገባ መብራት ስታጠፋ፤ የምድርን ሁላ መብራት ያጠፋችው
ይመስለኝ ነበር…
:
:
ከአባቴ በላይ የሚፈራና እውቀት ያለው
ሰው ያለ አይመስለኝም ነበር
.
.
እኔ ልጅ እያለው የሆነ ዛፍ አለ
በልጅነታችን ፍሬውን የጦጣ ፍራንክ ብለን የምንጠራው እሱ
እውነትም ጦጣዎች የሚገበያዩበት ይመስለኝ ነበር፣ በዛ ላይ
እሱን ፍሬ በጥንቃቄ ካስቀመጥከው ከ5 ቀን በኋላ ትክክለኛ
ሳንቲም ይሆናል ተብዬ ተሸውጃለው
.
.
ልጅ እያለው የሚጋረፉ አስተማሪዎቻችን ልጆች በሙሉ
በታቸው
አዳር የሚገረፉ ይመስለኝ ነበር
.
.
ሰፈራችን ያለ አንድ ልጅ በ ትምህርት
ነው ያበደው ሲባል የሁላችንም አጣ
ፈንታ ይመስለኝ ነበር
.
.
.
አቢዮት ጠባቂ ሲባል ቀበሌ ውስጥ አቢዮት የሚባል ውድ ህቃ
እንዳይጠፋ የሚጠብቅ ይመስለኝ ነበር
.
.
ትምህርት ጨርሼ ከ ፈረንጅ ጋር መንገድ
ላይ በ እንግሊዘኛ እያወራው መሄድ እፈልግ ነበር
.
.
እናቴ ማንበብ እና መጻፍ ያልቻለችው አጥኚ ብለው
የማይገርፉኣት ጥሩ ወላጆች ስለነበሩኣት ይመስለኝ ነበር
.
.
ኤሌትሪክ ደምህን መጦ ይገለሃል ስባል
ኤሌትሪኩ የመጠጠውን ደም የት እንደሚያጠራቅመው ግራ
ይገባኝ ነበር
.
.
አስተማሪዎች ከወንድ ጋር ሲያስቀመጡኝ ያባለጉኝ ይመስለኝ
ነበር
.
.
ማስቲካ የሚሰራው ከ ውሻ አንጀት ነው
ሰለሚባል ውሻ ባየው ቁጥር የሚታየኝ ሆዱ ውስጥ የያዘው
ማስቲካ ነው.
ይህች ምራቅ ሳትደርቅ ቶሎ መልዕክቱን አድርሰሽ ተመለሽ ስባል እውነት እየመሰለኝ የሁለት ኪሎ ሜትር
መንገድ ልቤ እስኪወል ስሮጥ ደርሸ እመለስ ነበር፡፡ በደርሶ መልስ አራት ኪሎ ሜትር ማለት ነውእናንተስ በልጅነታችህው ምን ይሰማችሁ ነበር?

Posted on 11-22-17, 01:58 pm


Karma: 100
Posts: 471/627
Since: 08-27-16

Last post: 41 days
Last view: 6 hours
በልጅነቴ፡ሰፈሬ፡የእስልምና፡ሐይማኖት፡የሚከተሉ፡ጎረቤቶች፡ነበሩ፡
ለታረድ፡የመጣውም፡በጋቸው፡በጉ፡እራሱ፡እስላም፡ይመስለኝ፡ነበር።

በጣም፡ልጅ፡ሆኜ፡እንደ፡ኮክ፣ብርቱካን፣ሙዝ፡ፖም፡የመሳሰሉ፡ፍሬዎች፡
በጣም፡እወድ፡ነበር። አባቴ፡ከሥራው፡ሲመለስ፡ሁልቀን፡ይዞልኝ፡ይመጣል።
አንድ፡ቀን፡ለካ፡ሥራ፡በዝቶበት፡ኖሮ፡አላመጣልኝም። የሰጠኝም፡ምክንያት፡
የሙዝ፡እናት፡ሞታ፡ቀብር፡ዋልን፡ብሎ፡ነግሮኝ፡እኔም፡በሃዘን፡አሳልፌአለሁ።
Pages: 1