ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing General Healthcare . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 11-12-17, 06:20 am


Karma: 100
Posts: 367/426
Since: 07-12-15

Last post: 34 days
Last view: 34 days
የልብና የደም ቧንቧ ጤና

በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ እና የተቀነባበሩ የፍራፍሬ ጭማቂዎች እና የአልኮል መጠናቸው አነስተኛ የሆኑ መጠጦች የምግብ ውህደትን እና የደም እንቅስቃሴን ያፋጥናሉ። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በተፈጥሮ የምናገኛቸው ምግቦች እና መጠጦችም የተዘጉ የደም ቧንቧዎችን በመክፈት ጤናማ የደም ዝውውር እንዲኖር በማድረግ ከልብ ህመም ይታደጋሉ።

1. አረንጓዴ ሻይ - በቀን አንድ ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት በደም ውስጥ የሚገኘውን ፈሳሽ መጠን ለማሳደግ እና የደም ቧንቧ መዘጋትን ለመከላከል ይጠቅማል። አረንጓዴ ሻይ ከዚህም በተጨማሪ የምግብ ውህደትን ለማፋጠንና የአተነፋፈስ ስርአትን ጤናማ ለማድረግ እንደሚረዳም ነው የተነገረው።

2. ቀረፋ - ይህ ጣፋጭ ቅመም ጎጂ የኮሊስትሮል መጠንን በመቀነስ ከልብ እና አተነፋፈስ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመከላከል ያግዛል።

3. ፕሪም - የጠቃሚ ኮሊስትሮል መጠንን የሚያሳድገውን ፕሪም ጭማቂ በየቀኑ መውሰድ፥ በአጠቃላይ የልብ ህመም የመጋለጥ እድልን በ40 በመቶ ለመቀነስ እንደሚረዳ ተነግሯል።

4. እርድ - እርድ የሰውነት መጉረብረብ እና መመረዝን ለመከላከል ሁነኛ ቅመም ነው። ከሰውነት መቆጣት ጋር ተያይዞ የደም ቧንቧዎች የመጠንከር ባህሪ ይታይባቸዋል። እናም በምግባችን ውስጥ እርድ መጨመር የደም ቧንቧዎቻችን ጤና ለመጠበቅ እና የደም መርጋትን ለመቀነስ ይረዳል ተብሏል።

5. አቮካዶ - በቀን ውስጥ ኦቮካዶን በተለያየ መንገድ የምንጠቀም ከሆነ ጤናማ የደም ኮሊስትሮል እንደሚጨምር ጥናቶች ያሳያሉ። ጤናማ ኮሊስትሮል የደም ቧንቧዎች መዘጋትን ለማስወገድ እንደሚረዳም ነው የሚነገረው።

6. ሮማን - የሮማን ፍሬ የደም ቧንቧዎችን ገበር መስራት (መወፈር) ይከላከላል። የዚህ ፍሬ ጭማቂም በሰውነታችን ውስጥ የናይትሪክ አሲድ መመረትን በማፋጠን የደም ዝውውርን ያሳድጋል፤ የደም ቧንቧዎችንም ክፍት ያደርጋል።

7. አበባ ጎመን - አበባ ጎመን በቫይታሚን ኬ እና ካልሲየም የበለፀገ መሆኑ ይነገራል። ይህም የደም ቧንቧዎችን ከጉዳት እንደሚታደግ ነው ጥናቶች የሚያሳዩት። በፋይበር ይዘቱ የተመሰከረለት አበባ ጎመን፥ የደም ግፊትን ለመቀነስ እና ጎጂ የኮሊስትሮል መጠንን ዝቅ ለማድረግም ያግዛል።

8. ለሚወዱት ሼር ያድርጉት፡፡

Pages: 1